Connect with us

ወጋገን ባንክ ያልተገባ የጦር መሳሪያ ክምችት ተገኘበት

ወጋገን ባንክ ያልተገባ የጦር መሳሪያ ክምችት ተገኘበት
Photo: Social media

ወንጀል ነክ

ወጋገን ባንክ ያልተገባ የጦር መሳሪያ ክምችት ተገኘበት

ወጋገን ባንክ ያልተገባ የጦር መሳሪያ ክምችት ተገኘበት

 

የፋይናንስ አገልግሎት ሰጭ በሆነው ወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ በዛ ያለ የጦር መሣሪያ ተከማችቶ መገኘቱ ተሰማ።

በአዲስ አበባ በርካታ የጦር መሳሪያ የተገኘባቸው ሌሎች ድርጅቶችም አሉ ተብሏል።

በወጋገን ባንክ  ዋና መሥሪያ ቤት የተገኙት የጦር መሣሪያዎች ለሌላ ዓላማ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል።

በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የነገሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር ናቸው ብለዋል፡፡ 

ሱር ኮንስትራክሽንም የተለያየ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሌላው የሕወሓት አካል ነው ተብሏል።

በእነዚህ መሥሪያ ቤቶች በሕዝብ ጥቆማ እና ኮሚሽኑ ካለው መረጃ በመነሳት ብርበራ እና ፍተሻ መደረጉን ሸገር ሰምቷል።

የጦር መሣርያ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን መከላከያ በራሱ ካምፕ ነው የሚያስቀምጠው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ በእነዚህ ተቋማት በብርበራ የተገኙትም ከፍተኛ የጦር መሣርያዎች ናቸው ብለዋል።

በከተማው ውስጥ ካሉ ባለሀብቶች መካከል ለሕወሓት ድጋፍ የሚያደርጉ እንደነበሩም ኮሚሽነሩ ለሸገር ነግረዋል፡፡ 

ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ንብረት ሊያፈሩ ይችላሉ ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ተጨባጭ መረጃ እና ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት በመፈፀም ተቀናጅተው የሚሠሩ አካላት ላይ ያተኮረ ሥራ ነው የሚያከናውነው ብለዋል፡፡

(ሸገር~ ተህቦ ንጉሴ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top