Connect with us

ህገወጥ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ህገወጥ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ወንጀል ነክ

ህገወጥ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ህገወጥ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያውቀው ህገወጥ ቆጣሪ በማስገጠም የኤሌክትሪክ ኃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ አምስት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት ፈልገው ለአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ ዲስትሪክት አመልክተው ተራ በመጠበቅ ላይ የነበሩ ቢሆንም፤ ጉዳዩን እኛ ያለወረፋ እናስፈፅምላችኋለን ብለው ነዋሪዎቹን የቀረቡ ደላሎች ከባለሙያ ጋር አገናኝተው ከተቋሙ ዕውቅና ውጪ 5 የኤሌክትሪክ ቆጣሪዎች እንዲገጠሙ በማድረግ በሃሰተኛ ደረሰኝ 78ሺህ 450 ብር እንዲከፍሉ አድርገዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ከቀናት ያህል የኃይል ተጠቃሚ ሆነው ቢቆዩም ቆጣሪው የቴክኒክ ችግር ስለነበረው ተጠቃሚዎቹ ይህንኑ ለተቋሙ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና የተቋሙ ባለሙያ ቦታው ድረስ በመሄድ ሲያረጋግጥ እንዳያገለግሉ የተወገዱ ቆጣሪዎች መሆናቸው መረጋገጡን በፖሊስ ምርመራ ተጠቅሷል፡፡

ፖሊስ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ የቀረበለትን አቤቱታ ተቀብሎ ባከናወነው ተግባር በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ የተቋሙ ሰራተኞች፣ ደላሎች እና በህገወጥ መልኩ የኃይል ተጠቃሚ የነበሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት በተለያዩ ብልሹ አሰራሮችና በመሰረተ ልማቱ ላይ በሚደረሱ ስርቆቶች ብቻ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለደንበኞቹ ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት በቴክኖሎጂ በተደገፈ አሰራር ጭምር በመጠቀም የተለያዩ ዘርፈ-ብዙ አሰራሮች የዘረጋ ቢሆንም፤ አንዳንድ ስነምግባር የጎደላቸው የተቋሙ ሠራተኞች፣ ደላሎችና ግለሰቦች መሰል ህገወጥ ተግባራት በመፈፀም የተቋሙን ስም በማጥፋት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ስለሆነም አገልግሎት ፈላጊ ደንበኞቻችን ማንኛውም አገልግሎት ከተቋማችን ስትፈልጉ ትክክለኛውን መንገድ በመከተል እንዲሆንና ብልሹ አሰራሮች ሲያጋጥማችሁ ደግሞ ለፀጥታ አካላት በመጠቆም እንዲሁም ለተቋማችን በአካል ድርስ በመምጣት እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top