Connect with us

10 ሺሕ ገጀራ ተያዘ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን

ወንጀል ነክ

10 ሺሕ ገጀራ ተያዘ

10 ሺሕ ገጀራ ተያዘ

ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10ሺ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡

በትላንትናው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከማህበረሰቡ የተሰጠውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ መርካቶ ውስጥ ጣና የገበያ ማእከል ጎን አድማስ ህንፃ ውስጥ አዲሱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ በሚፃረር መልኩ ተከማችቶ የተገኘው ከ10ሺ በላይ ጋጀራ በቁጥጥር ስር በማዋል ጠቅላላ ምርመራ እያካሄደበት እንደሆነ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሃኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡

የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባሎቻችንም ድርሻም የጎላ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በማሰራጨት ለሽብር አላማ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ የጦር መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ያሉት ሃላፊው ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወንጀለኛው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እንደካሄደበት ነው ብለዋል፡፡

የሽብርተኛ ቡድኖችን ተልዕኮ ለመፈፀም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ህዝቡ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተዘግቧል። (የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top