Connect with us

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ ንፁሃን ዜጎች  እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ 

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ ንፁሃን ዜጎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ
Photo: Social media

ዜና

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ ንፁሃን ዜጎች  እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ 

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ ንፁሃን ዜጎች  እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ 

 

የአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በመቶዎች የሚቆጠሩ እና ከጦርነቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡

በትግራይ አካባቢ የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች በመቋረጣቸው የጭፍጨፋውን ሙሉ መጠን ማወቅ አለመቻሉን የገለፀው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ በሁለቱም ወገን የሚፈጠረውን የህግ ጥሰት ይፋ ለማድረግ የተለያዩ አማራጮችን እየተጠቀመ እንደሆነም ገልጿል፡፡

ነገር ግን የአካባቢውን ነዋሪዎች በመጠየቅ አረጋገጥኩ ባለው የድርጅቱ መረጃ መሰረት በስለታማ ነገሮች የተገደሉ እና ተወግተው የተረፉ ዜጎች እንደተገኙ አመልክቷል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስከ አሁን ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ እንዳላረጋገጠ ገልጾ፣ ከአካባቢው ከነበሩት ምስክሮች ባገኘው መሰረት ጥቃቱን የፈፀሙት የህወሃት ቡድን ታማኝ የሆኑ ታጣቂዎች በፌዴራል ጦር ከተሸነፉ በኋላ ነው ብሏል፡፡

ድርጅቱ ሶስት ከጥቃቱ የተረፉ ዜጎችን አነጋግሮ በጽንፈኛው ህወሃት ቡድን ልዩ ኃይሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው እንደገለጹለት ጠቅሷል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጥቃቱ የተሳተፉ አካላትን ገለልተኛ ሆኖና መርምሮ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብም መንግስትን ጠይቋል፡፡

የህወሃት ቡድን መሪዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት በጦር ወንጀል ሊያስጠይቃቸው የሚችል በመሆኑ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ድርጅቱ አሳስቧል፡፡ (EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top