Connect with us

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በህገወጥ መንገድ ሊሄድ የነበረ ከ49 ሺህ በላይ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

Social media

ወንጀል ነክ

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በህገወጥ መንገድ ሊሄድ የነበረ ከ49 ሺህ በላይ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በህገወጥ መንገድ ሊሄድ የነበረ ከ49 ሺህ በላይ ዶላር ኮምቦልቻ ላይ በቁጥጥር ስር ዋለ

ነገሩ እንዲህን ነው ይላሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን! የሽብርተኛው ህወሃት የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሰጧቸውን ተደጋጋሚ የሰላም ዕድሎች መጠቀም ተስኗቸው እየፈፀሙ ያሉትን ትንኮሳና ወረራ እንደ ሽፋን በመጠቀም አንድ አንድ አካላት ከመሳሪያና ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ህግወጥ እንቅስቃሲዎችን ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡

ይሁንና እነዚህ አካላት የህዝባቸውንና የሀገራቸውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለመረጋገጥ ለአፍታም አይናቸውን ከማይከድኑት የደህንነትና የፀጥታ አካላት እይታ ውጭ መሆን አልቻሉም፡፡ ከእነዚህ አካላት ውስጥ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንቅስቃሴ ተጠርጥሮ ትናንት ምሽት ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለውን ዓሊ መሀመድ
አደምን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡

ዓሊ መሀመድ አደም ኮንቴነሮችን ከጅቡቲ አዲሰ አበባ የሚያመላልስ የከባድ መኪና አሸከርካሪ ነው፡፡ ግለሰቡ በቀን ነሃሴ 20/2013 ዓ.ም ማለዳ ላይ መደበኛ ስራውን ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ጅቡቲ ለማምራት ከመጀመሩ በፊት፤ በህገወጥ ጥቅም ከተሳሰረው ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ጎራ በማለት 49 ሺ 300 ዶላር (አርባ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ) በሚስጥር በመቀበል ወደ ጅቡቲ
የሚያደርገውን ጉዞ ይጀምራል፡፡

ዓላማውም ገንዘቡን ወደ ጅቡቲ በማጓጓዝ በጥቁር ገበያው ወይንም Black  Market በከፍተኛ ምንዛሬ በመቸብቸብ ትርፍ ማጋበስ ነው፡፡ ይሁንና ግለሰቡ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ሲደረግበት ስለነበር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ትናንት ከምሽቱ አምስት ሰአት ገደማ አካባቢ ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪው ዓሊ መሀመድ አደም አድርስልኝ ካለውና አዲስ አበባ ከሚኖረው መተዳዳሪያውን እንዲህ አይነት ህግወጥ የገንዘብ ዝውውር ከደረገው ግለሰብ የግንዘብ ጉርሻ በመቀበልናbተባባሪ በመሆን ጅቡቲ ለሚኖር ሌላ ተቀባይ አካል የአድራሽነት ሚና እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ያሰረዳሉ፡፡

የመረጃ ምንጮቻችን ከስፍራው የተጠርጣሪውን የዓሊ መሀመድ አደምን የወንጀል ድርጊት ያቀረቡልን፤ የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል እንዲሁም የዜጎችን ደህንነትና ሰላም ለማረጋገጥ የደህንነትና ፀጥታ አካላት እያደረጉ ያሉት ርብርብ በህዝቡ የተለመደ ትብብርና ተሳትፉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ለመግለፅvእንዲሁም የጁንታውንና የተባባሪዎቹን አከርካሪ ለመምታት መላው ህዝብና መንግስት ርብርብ እያደረጉ
ባሉበት በአሁኑ ወቅት በእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባር መሳተፍ ከሽብርተኝነት ተለይቶ የሚታይ አለመሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top