Connect with us

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ 

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ
Photo: ኢትዮ ኤፍ ኤም

ወንጀል ነክ

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ 

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ 

 

በአድዋ ድልድይ ስር የፈነዳው ፈንጂ፤ ፍተሻው በመጠንከሩ እጃቸው ላይ እንዳይገኝ የፈሩ የጣሉት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ አድዋ ድልድይ በሚባለው ቦታ ከጠዋቱ 2 ሰአት አካባቢ አንድ የታክሲ የረዳት ልጅ ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ ስር ገብቶ በነበረበት ወቅት በማዳበርያ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር አይቶ ምን ይሆን ብሎ ሲነካው እንደፈነዳ ተገልጧል፡፡

ልጁ ቀላል ጉዳት ደርሶበት ምኒሊክ ሆስፒታል እየታከመ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ለጣቢያችን እንደተናገሩት  የጸጥታ ሀይሉ ባጠቃላይ በጥምር ተደራጅቶ የቁጥጥር፣የፍተሻ እና ድንገተኛ የአሰሳ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የህዝቡ ጥቆማና የፀጥታ ሀይሉ ጠንካራ እንቅስቀሴ ያስጨነካቸውና ያስፈራቸው እጃቸው ላይ ጦር መሳርያ ያላቸው ሰዎች እየመጡ ከሚያስረክቡት ሌላ ፤ ውጪ እየጣሉ የሚገኙ እንዳሉ ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል። 

ዛሬ የተከሰተውም ከነዚህ ክስተቶች መካከልም አንዱ ነው ብለዋል።

በተለይ በአቃቂ ቃሊቲ፣በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣በኮልፌ ቀራኒዮ እና ወጣ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ይሄ ተስተውሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በተለያየ መንገድ እጁ ላይ ጦር መሳርያ ካለ እንዲያስረክብ ጥሪያቸውን ያቀረቡ ሲሆን አካባቢውን በጥንቃቄ መከታተሉን፣መጠቆሙን እና መሰል ቁሶችን በጥንቃቄ መመርመሩን እንዳይረሳ አሳስበዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ትኩስ ትኩስ ዜናዎችን፣ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top