Connect with us

ህወሓት ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው ዕለት በአማራ ክልል ይካሄዳል

ህወሓት ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው ዕለት በአማራ ክልል ይካሄዳል
Ethiopian Broadcasting Corporation

ወንጀል ነክ

ህወሓት ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው ዕለት በአማራ ክልል ይካሄዳል

ህወሓት ደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው ዕለት በአማራ ክልል ይካሄዳል

ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን  እየፈጸመው ያለውን ግፍ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ  ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት እንደሚካሄድ የአማራ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡

የክልሉ  መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ሰልፉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ “መላው የክልላችን ህዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ህገ ወጡ የትህነግ ቡድን ያደረሰውን ግፍ እና የሀገር ክህደት ወንጀል ለመላው ዓለም በምንችለው ሁሉ ለማሳወቅ የሰልፉ ተሳታፊ አንድንሆን ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

የሰልፉ ዓላማ ጽንፈኛው  የህወሓት ቡድን እየፈጸመው ያለውን ግፍና በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ክህደት ለመላው ዓለም ለማሳወቅ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሰልፉ ባህር ዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ እና ደብረ ታቦር ከተሞች ብቻ የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ባሉ የክልሉ ከተሞች ሰልፉ የማይካሄደው ህገ ወጡን  ቡድን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረገው ውጊያ ልዩ የጸጥታ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ሠላማዊ ሰልፉ ነገ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ተጀምሮ በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ በተዋቀረው የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እና የጸጥታ ኃይል ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት እንደሆነ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top