Connect with us

ላምሮት ከማል ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበች

ላምሮት ከማል ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበች
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ላምሮት ከማል ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበች

ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበች

ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል የፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በዛሬው ዕለት ለ4ኛ ጊዜቀርባለች።

ፖሊስ የጂ.ፒ.ኤስ ውጤት እየተጠባበቀ መሆኑን እንዲሁም በተሰጠው ቀጠሮ የሰው ምስክርና ሰነዶች ማሰባሰቡን ገልጿል።
ነገር ግን ከወንጀሉ ውስብስብነት አንፃር የሚጠበቁ ውጤቶች በመኖራቸው 14 ቀን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዋ ፈፅማለች የተባለውን የወንጀል ዝርዝር ለችሎቱ መግለፁ መረጃ ይጠፋል የሚል ስጋት ስለሚኖር ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ በቃል ጉዳዩን መዘርዘር አልቻለም። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ሊያጣራው ይችላል ብሏል። ጎን ለጎን የምርመራ መዝገቡን ዐቃቤ ህግ እየመረመረ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዋ በበኩሏ በወንጀሉ ተጠርጥረው ከተያዙት ሰዎች መካከል በወንጀሉ የተሳተፉትን በመለየት አብራቸው ፎቶ መነሳት መድረሷን ለፍርድ ቤት በመግለጽ በወንጀሉ ተጠያቂ አይደለሁም በማለት ገልጻለች። የዋስትና መብቷ እንዲከበርም ጠይቃለች።
የግራ ቀኙን የሰማው ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ተጨማሪ 6 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

#EBC

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top