Connect with us

ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ቅርቡ የደረሰውን ውድመት እና መልሶ ማቋቋም እየጎበኙ ነው

ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ቅርቡ የደረሰውን ውድመት እና መልሶ ማቋቋም እየጎበኙ ነው
Photo: Social Media

ዜና

ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ቅርቡ የደረሰውን ውድመት እና መልሶ ማቋቋም እየጎበኙ ነው

በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ የደረሰውን ጉዳት እና የመልሶ ማቋቋም ስራ በምን ተዟዙረው እየጎበኘ ነው።

ልዑካን ቡድኑ ጉብኝቱን ከምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ ከተማ ጀምሯል።በጉብኝቱም በምስራቅ ሸዋ ባቱ ከተማ በወቅቱ ውድመት የደረሰባቸውን መኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ተቋማትና ድርጅቶችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ይጎበኛሉ።

የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት የክልሉን መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን ጉብኝቱ በምስራቅ ሸዋ ባቱ፣ አርሲ ነገሌና ሻሸመኔን ጨምሮ የምዕራብ አርሲ፣ አርሲ እንዲሁም ባሌን ያካተተ እንደሚሆን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም ህብረተሰቡና የክልሉ መንግስት በቅንጅት እያከናወኑ ያለው የመልሶ ማቋቋም ስራ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ በዝርዝር ለመመልከትና ቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በተለይም የተፈናቀሉ ወገኖችና የወደመውን ንብረት ፈጥኖ ወደ ቦታው ለመመለስና ቋሚ ኑሯቸውን እንዲጀምሩ ብሎም የንግድ ተቋማቱ ጥገና ተደርጎላቸው ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ግብዓት የሚገኝበት መሆኑንም አቶ ጌታቸው አመልክተዋል።(መነሻ ምንጭ:- ኢኘድ )

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top