Connect with us

በአቶ ጃዋር እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ

“በአቶ ጃዋር መሐመድ እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ የጉምሩክ ሥርዓትን ሳይከተል ወደ ሀገር የገባ ነው” - ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

በአቶ ጃዋር እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ

“በአቶ ጃዋር መሐመድ እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ የጉምሩክ ሥርዓትን ሳይከተል ወደ ሀገር የገባ ነው” – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአቶ ጃዋር መሐመድ እጅ የተገኘው የሳተላይት መሣሪያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሳይፈፀምበት ወደ ሀገር የገባ መሆኑን አስታወቀ።

ሳተላይቱ የኢትዮ-ቴሌኮም ኔትወርክ ተቋርጦም ከ5 እስከ 25 ኪ.ሜ በሚገኝ ርቀት ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ እንደነበርም በባለሙያ ተረጋግጧል ብሏል።

ይህ የሳተላይት መሣሪያ በግለሰቦች እጅ ሊገኝ የማይገባ እና ፈቃድ ያላገኘ መሆኑን ነው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያስታወቀው።

በሌላ በኩል የድምፃዊ ሀጫሉን ሞት ተከትሎ ከተጠርጣሪዎች የተገኙ ዘጠኙም የሬዲዮ መገናኛዎች ከኢትዮ-ቴለኮምም ሆነ ከሌሎች ሥልጣን ካላቸው የመንግሥት ተቋማት ፍቃድ የሌላቸው መሆናቸውንም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጠቁሟል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top