Connect with us

በእነጀዋር መሐመድ ጉዳይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቀደ

በእነጀዋር መሐመድ ጉዳይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቀደ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

በእነጀዋር መሐመድ ጉዳይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቀደ

አቶ ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእሰር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል።

በዚህ ጊዜ የተከሳሽ ጠበቆች ደንበኛቸው ምግብ ከቤተሰቡ የሚቀርብለት ቢሆንም ግንኙነታቸው በርቀት በመሆኑ ባለበት ከርቀት አይቶ የመለየት ችግር ቤተሰቦቹን በቅርበት እንዲያገኝ እንዳልተፈቀደለት ለችሎቱ አቤት ብለዋል።

ፖሊስም ይህንን በተመለከተ በሰጠው ምላሽ ታሳሪዎችና ጠያቂዎች መካከል መቀራረብ እንዳይኖር የተደረገው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጣጠር በወጣው ደንብ መሰረት መሆኑን ጠቅሶ ምላሽ ሰጥቷል።

በተጨማሪም አቶ ጃዋር ታስረው የሚገኙበት ክፍል በቂ ብርሃን የሌለው መሆኑና መጸዳጃ ቤት የመጠቀም ችግርን በማንሳት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ደንበኛቸው ጥፋተኝነታቸው ገና ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ምስላቸው እየቀረበ ዘገባዎች እንደሚቀርቡና ፍርድ ቤቱም ይህንን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ለእስረኞች መጸዳጃ ቤትን በተመለከተና በማረፊያ ክፍሎች ውስጥ ያለውን ብርሃን በተመለከተ አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲያደርግ ያዘዘ ሲሆን፤ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ስለቀረበው አቤቱታም ጠበቆች ያሏቸውን ተቋማት በስም ለይተው እንዲያቀርቡ አዟል።

በዚህም መሰረት ፖሊስ ለምርመራ የጠየቀውን የ14 ቀናት ጊዜ ፈቅዶ ጉዳዩን ለመመልከት ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ አብቅቷል።(BBC)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top