Connect with us

ፍርድቤቱ የእነጀዋርን በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ በአስተዳደር እንዲታይ ወሰነ

እነስብሀት ነጋ ቂሊንጦ ሊወርዱ ነው
የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ

ወንጀል ነክ

ፍርድቤቱ የእነጀዋርን በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ በአስተዳደር እንዲታይ ወሰነ

ፍርድቤቱ የእነጀዋርን በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ በአስተዳደር እንዲታይ ወሰነ

 የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የዐቃቤ ህግን መቃወሚያ ለመስማት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዐቃቤ ህግ መቃወሚያውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

በዚ ችሎት ላይ ተከሳሾች አቶ ጀዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ወደ ችሎቱ ያልቀረቡ ሲሆን ለዚህም፤ በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዲሁም ባለን ፖለቲካዊ ተሳትፎ የተነሳ እንዲሁም በማረሚያ ቤቱ እና በፍርድ ቤት መሀከል ያለው እርቀት ሰፊ በመሆኑ ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ፈጥሮብናል፤ በዚህ ምክንያትም መቅረብ አልቻልንም በመሆኑም በቀጣይ ለሚኖረው የፍርድ ሂደት በአቅራቢያችን ጊዜያዊ ችሎት  ይቋቋምልን የሚል አቤቱታቸውን በጠበቆቻቸው በኩል በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

ከዚህም ሌላ ዐቃቤ ህግ 11ኛ ተከሳሽ አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ 14ኛ ተከሳሽ አቶ ብ/መስቀል አበበ እና 15ኛ ተከሳሽ አቶ ፀጋዬ ረጋሰ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማድረግ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሊቀርቡ ስላልቻሉ በሌሉበት ክሳቸው እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት ጠይቆ፤ ተከሳሾች በተቋሙ ላይ ላቀረቡት ቅሬታ በፅሁፍ ምላሽ መስጠቱን ገልጾ ነገር ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ እንዲቀርቡ የተፃፈ ትዕዛዝ ባለመኖሩ ሊቀርቡ አለመቻላቸውን አስረድቷል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌዴራል 1ኛ የፀረ ሽብርና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ችሎት፡-

  1. በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ተከሳሾችን በሚመለከት ክሳቸው በሌሉበት እንዲታይ ወስኗል፤
  2. በሌላም በኩል እነ አቶ ጀዋር መሀመድ ያቀረቡትን ጊዚያዊ ችሎት ይቋቋምልን ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር አቅርቦ ምላሽ እንዲሰጥበት እንደሚደረግ፤
  3. ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በግለሰብ ደረጃ ቀርበው ምላሽ ይስጡበት ለሚለው የተከሳሾች ቅሬታ ላይ ለትዕዛዝ ለመስጠት በሚድያ ቀረበ የተባለው አስተያየት በእንግሊዘኛ እና አማርኛ ኮፒ ተደርጎ በሲዲ ከቀረበ በኋላ ትዕዛዝ የሚሰጥበት መሆኑን በመግለፅ  ቀጣዩን ቀጠሮ ለታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ.ም በማድረግ የእለቱ ችሎት ተፈፅሟል፡፡(የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top