Connect with us

እንደ አቶ ፒ ይባርከን ?… !

እንደ አቶ ፒ ይባርከን ?... !
Piqsels

አስገራሚ

እንደ አቶ ፒ ይባርከን ?… !

እንደ አቶ ፒ ይባርከን ?… !
(አለማየሁ ገበየሁ ~ እንግሊዝ)

የ 101 አመት እድሜ ያላቸው ኢጣሊያዊ አዛውንት ከኮሮና ቫይረስ አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል፡፡ The Local የተባለው ጋዜጣ የሪሚሲ ከተማን ም/ከንቲባ ግሎሪያ ሊሲን ጠቅሶ እንደዘገበው አቶ ፒ / ባለስልጣናቱ ለግዜው የሰጧቸው ስም ነው / የተወለዱት አለም በስፓኒሽ ኢንፍሎዌንዛ ወረርሽኝ ክፉኛ በተደቆሰችበት በ 1919 ነበር፡፡

እኤአ ከ 1918 እስከ 1920 የቆየው ይኸው ወረርሽኝ 5 መቶ ሚሊየን ህዝቦችን አጥቅቶ ክ17 ሚሊየን በላዩን መግደሉ ይታወሳል፡፡ በኢጣሊያ ብቻ 6 መቶ ሺዎች ተሰውተዋል፡፡ በወቅቱ የሁለት አመት እድሜ የነበራቸው የዛሬው አቶ ፒ ታዲያ፣ ዘመድ አዝማዳቸውን ሲያጡ ከዚህ ደዌ በተአምር ተርፈዋል፡፡ አቶ ፒ ባሳለፉት መቶ አመታት አሰቃቂ ጦርነቶችን / የአለም ጦርነት አንድና ሁለት፣ አስከፊ የረሃብ፣ የውድቀትና የሰቆቃ ዘመናትን በተቃራኒው ደግሞ የፍሰሃ ዘመናትን አይተዋል፡፡ አለም በተለያዩ ምክንያቶች ያፈራችውን ገፈት የተቋደሱት አቶ ፒ ዛሬም በቃህ አልተባሉም፡፡ የግዜው ወረርሽኝ በሆነው ኮሮና ቫይረስ ተጎብኝተዋል:፡

የወቅቱ ሳይንሳዊ ጥናት ከ 70 አመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዙ አጥብቆ ይመክራል፡፡ በሽታን የመከላከል አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ የመዳን ተስፋቸው ያጠራጥራል በሚል፡፡ ለዛም ነው የኢጣሊያ ዶክተሮች አቶ ፒ በህይወታቸው የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ከተፋጠጡት ኮሮና ቫይረስ ሊያመልጡ አይችሉም ብለው የገመቱት ፡፡ ሳያንስ ያስባል… ፈጣሪ ፍቃድ ይሰጣል እንዲሉ፣ አቶ ፒ ልክ እንዳለፈው 100 አመታት ዛሬም ወረርሽኙን ድል ነስተው ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

ሲጠቃለል አዛውንቶች ሁሉ አይድኑም ፣ ወጣቶች ሁሉ የስጋት ቀጠና ውስጥ አይወድቁም ብሎ መደምደም አይቻልም ፡፡ አዛውንትም ሲድን ወጣትም ሲሞት ታይቷልና፡፡ እዚህ ሁሉ የማይረባ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት እንደ አቶ ፒ ይባርከን ማለት አንድ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ብርክናውን ለማግኘት ግን ሁለተኛው ነገር ይኸው …

  • እጅዎትን ደጋግመው ይታጠቡ  – ካልታጠቡ ፊትዎን አይነካኩ
  • ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ ሶፍት ወይም እጅጌዎን ይጠቀሙ
  • ቤትዎ ይሰብሰቡ
  • ከቤት ከወጡ ፈቀቅታን ይተግብሩ 

Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top