Connect with us

ኮሮና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኮሮና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል
Photo: Social media

ዜና

ኮሮና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኮሮና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

      ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ የመተንፈሻ መሳሪዎች እጥረት እጅግ አሳሳቢ ሆኗል

በኮሮና ቫይረስ ታመው ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ የመተንፈሻ መሳሪዎች እጥረት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የኮሮና ህክምና ማዕከላት ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

ከመሳሪያዎች እጥረት ባለፈም ላሉት የመተንፈሻ መሳሪያዎች የመለዋወጫ እቃዎች  ባለመኖራቸው ችግሩን ይበልጥ አስከፊ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ 19 ህክምና ማዕከል የፅኑ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ህሩይ አርዓያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር ከቀን ቀን እያሻቀበ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከምንግዜውም  በላይ ጨምሯል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ ካሉት 22 የፅኑ ህክምና አልጋዎች ውስጥ ሁሉም መያዛቸው የሚገልጹት ዶክተር ህሩይ ከእነዚህ ውስጥም 65 በመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

የሚሊንየም ኮቪድ 19 ህክምና ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ በበኩላቸው፣  የማህበረሰቡን መዘናጋት ተከትሎ አሁን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን  ይናገራሉ፡፡

በዚህ ሳቢም  ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ሁሉንም  ጽኑ ህሙማን ማስተናገድ አለመቻሉን   የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፣ በተለይም  የመተንፈሻ መሳሪዎችን እገዛ የሚፈልጉ ህሙማን መበራከታቸው  ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል ያሉት  የመተንፈሻ መሳሪያዎች ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ አገልግሎት የሰጡ በመሆናቸው አሁን ላይ ያላቸው አቅም ዝቅተኛ መሆኑን ያብራራሉ፡፡

የኮሮና ታካሚዎች መብዛት የህክምና ማዕከላትን ከማጨናነቁ ባለፈ በባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም ዜጎች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች በትክክል ገቢራዊ እንዲያደርጉ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

ፎቶ፡- ኢንተርኔት

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top