Connect with us

ግሸን ከታሪክ ጋር

ግሸን ከታሪክ ጋር
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ግሸን ከታሪክ ጋር

ግሸን ከታሪክ ጋር፡፡
****
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የግማደ መስቀሉ ማረፊያ ስለሆነችው ታሪካዊቷ ግሸን ማርያም ትረካውን ጀምሯል፡፡ ግሸን ከታሪክ ጋር ሲል የቦታውን ታሪክ ከትናንት እስከ ዛሬ በአጭሩ ያስቃኘናል፡፡ መልካም ንባብ |  ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ግሼን ብዙ ነገራችን ናት፡፡ ምስጢር፣ እውቀት፣ እውነት፣ ውበት፣ እምነት፣ ታሪክ፡፡ ዛሬ ታሪኳን እናነሳለን፡፡ ስንነሳ ግር እንዳይል፤ የምንጽፈው ስለ ታላቋ ደብር ግሼን ደብረ ከርቤ ነው፡፡

አምባሰል የሙዚቃ ማማ የመሰለው ካለ ሌላ አልሰማም፡፡ አምባሰል ማማ ግሼን ናት፡፡ የግሼንን ታሪክ ስንፈትሸው ከካሌብ ያገናኘናል፡፡ ካሌብ ጋር ደርሶ መቆም የለም፡፡ ደግሞ ባህር እንሻገራለን፡፡ እስከ የመን፡፡ ናግራን ደርሰን ስንመለስ ግሼንን ከታሪክ ጋር እንዘክራታለን፡፡

ዐጼ ካሌብ ገናና የአክሱም ንጉሥ ነው፡፡ ኢትዮጵያን በሰላም ማስከበር ታሪክ ስናነሳት ከዓለም ትቀድም ነበር የሚያስብል ታሪክ እንዲኖረን ያደረገ ጀግና፡፡ የጦር አውዶቹ ሩቅ ናቸው፡፡ እኔ የመጠራውን በለው እንደ ድንቅ ጀብድ አላየውም፡፡ የራቀውን እቆጥራለሁ፡፡ ባህር የሚሻገሩ የድል ታሪኮችን፡፡ ከዚያ አንዱ ናግራን ነው፡፡ ደቡብ አረቢያ፡፡ ንጉሡ ዱነዋስን ፊንሐስ፤ ችግሩ በደልና ስቆቃ፡፡ ያኔ ነው ናግራን መዝመት ያስፈለገው፡፡

አክሱማውያን የዘገነም አዘነ ያልዘገነም አዘነ በሚሉባት የተረክ ዋሻ ሩቅ ዘመተ፡፡ ለድልና ሰላም ለማስከበር:: እርሱ ስሙ ካሌብ ዝናው ገናና የኾነ ንጉሥ ነው፡፡ ንጉሡ ጥበበኛ ነው፡፡ ዛሬ ላሊበላን ኢትዮጵያዊ አልሰራውም ለሚሉ አያሌ ውቅሮችን አስቀድመው እውን በማድረግ ውቅር እያየ ያደገ ውቅር መስራቱን የምናመሳክርባቸው ናቸው፡፡ የጉባ ላፍቶዋ ይአኑባ ማርያም፣ የላስታዎቹ የብልባላ ውቅሮች፣ የቡግናው ሆር ሆር፣ ብቻ ብዙ ናቸው፡፡ ሊያውም ድንቅ ውቅር ቤተክርስቲያናት፡፡

ግሼን ማርያም ከታሪኩ ታሪኳን ያገናኘች ታላቅ ስፍራ ነች፡፡ ናግራን ድል አድርጎ ወደ ሀገሩ ሲመጣ ከአረብያ ተከትለውት ከመጡ አባቶች አንዱ አባ ፍቃደ ክርስቶስ የተባሉ መነኩሴ ነበሩ፡፡ ከናግራን ሁለት ጽላቶችን ይዘው የመጡት አባ ፍቃደ ክርስቶስ በሽሎን ተሻግረው ግሸንን ሲመለከቱ የአምባው ተፈጥሮ አስደነቃቸው ይላል የመጽሐፈ ጤፉት መግቢያ፡፡ የግሼን አምባ ድንቅ ተፈጥሮ ነው፡፡ ገደሉ ደግሞ ንብ የሞላው ማር እንደ ጤዛ የሚያንጠባጥብ ነበር ይላል ታሪኩ፡፡ እኒህ አባት ናቸው፡፡ ይኼን አይተው አምባ-አሰል ያሉት፡፡ አምባ ከፍታውን አሰል ማለት ማሩን ገልጾ ስሙ የማር አምባ ተባለ፡፡

ግሼን ደብረ ከርቤም በዐፄ ካሌብ ጊዜ ተመሰረተች፡፡ ደብረ ነገሥት ለምን ተባለች? ደብረ ነጎድጓድ ያላት ማን ነው? ደብረ እግዚአብሔርስ፤ እየሮጥን እንተርከዋለን፡፡ በልኩ ብንናገረውም መኖር አይበቃውምና፤ ስለወደድኩት የተጠቀምኩት የሩት ራስታን ምስል ነው።

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top