Connect with us

የአለማችን እጅግ ውዱ የፊት ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተተምኗል

የአለማችን እጅግ ውዱ የፊት ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተተምኗል
Photo: Social Media / An 18 carat gold, diamond-encrusted mask. Courtesy of Yvel.

አስገራሚ

የአለማችን እጅግ ውዱ የፊት ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተተምኗል

በእስራኤል የሚገኝ አንድ ታዋቂ የጌጣጌጥ አምራች ኩባንያ በአለማችን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የተተመነለትን እጅግ ውድ የፊት ጭምብል ባለፈው እሁድ ለእይታ ያበቃ ሲሆን፣ የጭምብሉ የመሸጫ ዋጋ 1.5 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ያቬል የተባለው ኩባንያ እያመረተው የሚገኘው ይህ የፊት ጭምብል ከ18 ካራት ነጭ ወርቅ የተሰራና በ3 ሺህ 600 ደቃቅ የአልማዝ ፈርጦች የተንቆጠቆጠ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ጭምብሉ በቀጣዩ አመት ተጠናቅቆ ለሽያጭ እንደሚበቃም አመልክቷል፡፡

ኩባንያው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያመርተውን ይህንን እጅግ ውድ ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር መዥረጥ አድርጎ ለመግዛት የፈቀደ ገዢ መገኘቱን የጠቆመው ዘገባው፣ በአሜሪካ የሚኖር ቻይናዊ ነጋዴ ከመሆኑ ውጭ ስለ ግለሰቡ ተጨማሪ መረጃ አልሰጠም፡፡

የአለማችን እጅግ ውዱ የፊት ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ተተምኗል

በእስራኤል የሚገኝ አንድ ታዋቂ የጌጣጌጥ አምራች ኩባንያ በአለማችን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የተተመነለትን እጅግ ውድ የፊት ጭምብል ባለፈው እሁድ ለእይታ ያበቃ ሲሆን፣ የጭምብሉ የመሸጫ ዋጋ 1.5 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

 

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአለም ህዝቦች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እየተመቱና ለስራ አጥነት እየተዳረጉ በሚገኙበት አስቸጋሪ ወቅት ላይ ለአንድ ጭምብል 1.5 ሚሊዮን ዶላር ግፍ ነው የሚሉ አስተያየቶች መደመጣቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ ጭምብሉ 270 ያህል ግራም ክብደት ያለው ከመሆኑ ጋር በተያያዘ፣ ኮሮናን ለመከላከል በፊት ላይ አጥልቆ ለመንቀሳቀስ አመቺ ላይሆን እንደሚችል መነገሩንም አክሎ ገልጧል፡፡

Click to comment

More in አስገራሚ

  • ነፃ ሃሳብ

    ዛሬ ዓለም የስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፤

    By

    ዛሬ ዓለም የስደተኛ ወፍ ቀንን ያከብራል፤ ስለ ስደተኛ ሰው ክብር እያሰብን እናከብረዋለን (ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)...

  • "የመንግስትን ውሳኔ እደግፋለሁ" ክቡር ገና "የመንግስትን ውሳኔ እደግፋለሁ" ክቡር ገና

    ነፃ ሃሳብ

    “የመንግስትን ውሳኔ እደግፋለሁ” ክቡር ገና

    By

    “የመንግስትን ውሳኔ እደግፋለሁ” ክቡር ገና መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ድርሻ ወደ ግል የማዞር እንቅስቃሴውን ለጊዜውም ቢሆን...

  • ግሸን ከታሪክ ጋር ግሸን ከታሪክ ጋር

    ባህልና ታሪክ

    ግሸን ከታሪክ ጋር

    By

    ግሸን ከታሪክ ጋር፡፡ **** ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የግማደ መስቀሉ ማረፊያ ስለሆነችው ታሪካዊቷ ግሸን ማርያም ትረካውን...

  • እጅ እነሳለሁ!! እጅ እነሳለሁ!!

    ባህልና ታሪክ

    እጅ እነሳለሁ!!

    By

    #እጅ_እነሳለሁ!! (አስራት በጋሻው) ቦይንግ ሰራሹ ማክስ 737 አውሮፕላን ወድቆ በውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በሙሉ ከሞቱ በኃላ...

  • ዳግም ውልደት ዳግም ውልደት

    አስገራሚ

    ዳግም ውልደት

    By

    ንስር እስከ ሰባ ዓመት በሕይወት የመኖር ጸጋ ተሠጥቶታል። ነገር ግን ይህን የ70 ዓመት የዕድሜ ፀጋ አጣጥሞ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top