Connect with us

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ተማሪዎችን ሸለመ

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ተማሪዎችን ሸለመ
አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን

ዜና

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ተማሪዎችን ሸለመ

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ተማሪዎችን ሸለመ

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና አጋሮቹ ከአፍሪ ኼልዝ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ኮቪድ 19ን መከላከል ላይ ትኩረቱን ባደረገው “አሪፎቹ” የተሰኘ ፕሮግራሙ ተማሪዎችን እያዝናና ስለ ኮሮና ወረርሽኝ ግንዛቤ ሲያስጨብጥ ቆይቷል።

ይህ ፕሮግራም ለ3 ወራት በየሳምንቱ ከሰኞ እስከ አርብ ሲተላለፍ ነበር።

ፕሮግራሙ ስለ ኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች በተለያዩ አቀራረቦች ሲተላለፍ የቆየ ሲሆን ለተማሪዎች አርአያ የሚሆኑ ከሀገር ውስጥና ከውጪው አለም ጀግና የሚባሉ ሰዎች ታሪክ በማራኪ አቀራረብ  ሲቀርብ ቆይቷል።

 በተያያዘም ተማሪዎች ተመልካች ብቻ ሳይሆኑ ተሳታፊ ጭምር እንዲሆኑ በእየዕለቱ ፕሮግራም ማብቂያ ላይ ምን ያህል እንደተከታተሉ ለማወቅ የሚያሸልሙ ጥያቄዎች ይጠየቁ ነበር።

ተማሪዎቹም በ8455 ጥያቄ በመመለስ ተሳታፊ ነበሩ።

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን ለሁለተኛ ጊዜ በአዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራሙ በተደጋጋሚ ጥያቄ በትክክል ሲመልሱ ለነበሩ ተማሪዎች የብስክሌት፣ የትምህርት ቤት ቦርሳ እና የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች ሸልምዋል።

ተሸላሚዎች ከተለያየ የሀገሪትዋ ክፍል የመጡ ሲሆን ሽልማቱን ያበረከቱት ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ ናቸው፡፡

ዶ/ር ዮሐንስ በሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የዚህ አይነት አስተማሪ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እና ህብረተሰቡን ከኮቪድ ወረርሽኝ እራሱን እንዲጠብቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡

አፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን አሪፎቹ ፕሮግራምን ከጀመረ አንስቶ 215 ተሳታፊ ተማሪዎችን በመሸለም ማበረታታቱን ተገልጽዋል፡፡

ይህን የሽልማት ዝግጅት ለየት የሚያደርገው ተሸላሚዎቹ ከቦንጋ፣ ደሴ፣ አርባምንጭ፣ ሀዋሳ እና ሌሎች ራቅ ያሉ የሀገሪትዋ ክፍሎች ለሽልማት መምጣታቸው እንደሆነም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪኸልዝ ቴሌቪዥን መስራች ዶ/ር ሜሎን በቀለ በበኩላቸው ፕሮግራሙ በርካታ ተመልካቾችን በማስተማር ፣ በማዝናናት እና በማሳተፍ ውጤታማ በመሆኑና በተመልካቾች ጥያቄ መሠረት ፕሮግራሙ ቀጣይነት እንዲኖረው እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በአዲስ የኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያው ጭምር ለማስተላለፍ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪኸልዝ ኤፍ ኤም 93.8 ራዲዮ ጣቢያ ከታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ አዝናኝ ስርጭቱን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top