Connect with us

መሬት ያልወረደው የመንግስት ውሳኔ

መሬት ያልወረደው የመንግስት ውሳኔ
Photo Facebook

ወንጀል ነክ

መሬት ያልወረደው የመንግስት ውሳኔ

መሬት ያልወረደው የመንግስት ውሳኔ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹን ያድርሱ ቢልም ግቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚሉ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ሆነዋል፡፡

የመንግስት መኪና ትራንስፖርት ይስጡ ቢባልም አደባባዮቹ ላይ አገልግሎቱን የሚሰጡ ትራንስፖርቶች አይታዩም፡፡

የፌዴራሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንደ ሀገር ተከታታይ እርምጃዎችን ይፋ እያደረገ ነው፡፡ የመንግስት ውሳኔ ብዙዎቹ ተግባራዊ ሲሆኑ ግን እየታዩ አይደለም፡፡ ስብሰባዎች እንዲቀሩ ከተደረጉ በኋላ የብልጽግና ፓርቲ የታችኛው መዋቅር ስብሰባዎች ቀጥለው ሰንብተው ነበር፡፡

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን መጨናነቅ ለመቅረፍ በትራንስፖርት ዘርፍ ያለው ችግር እንዲፈታ የመንግስት መኪኖች አገልግሎት በነጻ ይሰጣሉ ቢባልም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ዛሬም ትራንስፖርት በሚጠብቁ ሰልፈኞች ተጨናንቀዋል፡፡ የመንግስት መኪኖች ይህንን ችግር ለመፍታት ወደ ስፍራው ሲመጡና አገልግሎት ሲሰጡ አይታዩም፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ችግሩ ለመቆጣጠር ተማሪዎቻቸው ከቤተሰቦቻቸውን ጋር እንዲቆዩ የተወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ተማሪዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርት እንዲሸኙ የሚል መግለጫ ቢወጣም እስከ እዚህ ቀን ግቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚል ማስታወቂያ በመለጠፍ የትራንስፓርት አማራጩን ያላስቀመጡ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ሆነዋል፡፡
.
በመኖሪያ አካባቢዎች የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ ፕሌይ ስቴሽንና ፑል ማጫወቻዎች በተዘጋው ትምህርት ምቹ ጊዜ ላገኙ ወጣቶች የስጋት ማሳለፊያዎች ሆነዋል፡፡ ኤርፖርት አካባቢ የተሰማው ኳራንታይንን የማስመለጥ ዜናም አሉባልታ ይሁን እውነታ የሚያረጋግጥ መረጃ አልተሰጠም፡፡ ይህም ሀገራዊ የዜጎች የደህንነት ስሜት ላይ የሚፈጥረው ጫና ግምት ውስጥ አለመግባቱን ያሳያል፡፡

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top