Connect with us

መረጃ አዘል ጥያቄ | ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ

መረጃ አዘል ጥያቄ | ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ
Photo: Facebook

ወንጀል ነክ

መረጃ አዘል ጥያቄ | ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ

መረጃ አዘል ጥያቄ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ለዩኒቨርሲቲዎች ባስተላለፈው ሰርኩላር ካስቀመጣቸው ቁምነገሮች ተከታዩ ይጠቀሳል።

“ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ፊት ለፊትና በክፍል የሚሰጡ ትምህርቶችን በማስቀረት ለተማሪዎች handout, reference books, online, soft copy materials ወ.ዘ.ተ በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግላቸዉ/ በመኝታ ክፍላቸዉ ሆነዉ እንዲያነቡ ይደረግ፣ መምህራን በኢሜይልና በተለያዩ ስልቶች የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲያስቀጥሉ ይደረግ፣ ይህ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን በየደረጃዉና በተዋረድ ክትትል ይደረግ”ብሏል።

#ጥያቄ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበጀት በሰው ኃይል በቂ ዝግጅት ባላደረጉበት፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የአስተዳደር አካላት በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ባልመከሩበት ሁኔታ እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ባለበት፣ ኢንተርኔት ባለባቸው አካባቢዎች ተማሪዎች በክፍላቸው እንደዋይፋይ ያሉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች በሌሉበት ሁኔታ… ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው እየዋሉ ሊማሩ የሚችሉበት ተጨባጭና የተመቻቸ ሁኔታ ይኖራልን? በጨዋ ደንብ ሀሳብ እንስጥበት?

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች
ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ስጋት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሀገራችንም እስከ አሁን አምስት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ተረጋግጦ ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሆነና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመግታት መንግስት መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅትም በሽታው ወረርሽኝ መሆኑን ካወጀበት ጊዜ አንስቶ ለጥንቃቄ ይጠቅማሉ ብሎ ካስቀመጣቸው መፍትሄዎች መካከል የሰዎች መሰባሰብን የሚሹ ጉዳዮችን ማስቀረት ይገኝበታል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ በመሆናቸው ተቋማቱን ዘግቶ ተማሪዎቹን ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ እየተወሰዱ ካሉ ጥንቃቄዎች አኳያ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንዳሚያመዝን ታምኖበታል፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በሚሄዱበት ጊዜ በጉዟቸው ለቫይረሱ የመጋለጣቸው እድል ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ስለሆነም ባሉበት ሆነው ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ መመሪያዎችን ተከትለው ጥንቃቄ በማድረግ በመምህራኖቻቸው የሚሰጡ ንባቦችን እያካሄዱ ለ2 ሳምንታት የሚቆዩ ይሆናል፡፡

ይህም ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ

1. ለተማሪዎች አስፈላጊው ክትትል ይደረግ

2. ፊት ለፊትና በክፍል የሚሰጡ ትምህርቶችን በማስቀረት ለተማሪዎች handout, reference books, online, soft copy materials ወ.ዘ.ተ በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም በግላቸዉ/ በመኝታ ክፍላቸዉ ሆነዉ እንዲያነቡ ይደረግ፣ መምህራን በኢሜይልና በተለያዩ ስልቶች የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲያስቀጥሉ ይደረግ፣ ይህ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን በየደረጃዉና በተዋረድ ክትትል ይደረግ

3. ተማሪዎች እጃቸዉን አዘውትረውና በተደጋጋሚ በሳሙና በመታጠብ ንጽህናቸዉን እንዲጠብቁ ለማድረግ ተቋማት በአስቸኳይ የሳሙና፣ ሳኒታይዘር እና አልኮል አቅርቦቶችን በመግዛት ተደራሽ እንዲያደርጉና እንዲያሰራጩ ይደረግ፣

4. በቤተ መጽሃፍትና በመመገቢያ አዳራሾች መተፋፈግን ለማስቀረት የመቀመጫዎች ጥግግት እንዳይኖር ይደረግ፣ መጨናነቅ እንዳይኖርም የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ይራዘም፣

5. ኮንፍረንሶች፣ ወርክሾፖች እና ስብሰባዎች እንዳይኖሩ ይደረግ፤ ቀድም ብለው የታቀዱም ካሉ ይሰረዙ፣ ግድ የሚሉ ስብሰባዎች ሲያጋጥሙ ቅርርብና ጥግግት ሳይኖር ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ይከናወን፣ እንዲሁም ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ይካሄድ፣

6. ስለቫይረሱ ግንዛቤ የሚፈጥሩ መልዕክቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ግቢዎች ውስጥ ተደራሽ ይደረጉ

7. በየተቋማችሁ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን የሚከታተል አንድ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ክትትል ይደረግ፡ የቫይረሱ ምልክት የታየባቸውን ለመጠቆም የሚያስችሉ ስልክ ቁጥሮች በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተዘጋጅተው ጥቆማዎችን የሚቀበሉና ለበላይ አመራሩ ሪፖርት የሚያደርጉ ይሁን

በመሆኑም በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመጋቢት 8/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ሳምንታት ቀጣይ አቅጣጫ እስከሚሰጥ ደረስ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ያሉትን በየተቋሞቻችሁ ተግባራዊ እንድታደርጉ በጥብቅ አሳስባለሁ፡፡

ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top