Connect with us

ፍርድ ቤቱ የአቶ ጃዋር መሐመድን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ

ፍርድ ቤቱ የአቶ ጃዋር መሐመድን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ፍርድ ቤቱ የአቶ ጃዋር መሐመድን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ

በወንጀል ጉዳይ የተጠረጠሩት አቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገ።

ተጠርጣሪው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የአራዳ ተረኛ ወንጀል ችሎት ላይ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን በመግለጽ ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪው ላይ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እንደከፈተባቸው አስታውቋል። በመሆኑም የምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ ጠይቋል።

የተጠርጣሪው ጠበቃ በበኩላቸው በደንበኛቸው ላይ ፖሊስ ባካሄደው የምርመራ ስራ ያገኘው ውጤት ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲጠበቅ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ጉዳዩን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው ወደ ፊት ክስ የሚመሰረትባቸው ከሆነ የተጠረጠሩበት መዝገብ የሰው ሕይወት የጠፋበትና ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

ተጠርጣሪው ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት መብታቸውን መጠየቅ እንደሚችሉ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡ ተዘግቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ ለማሰማት መዝገብ አስከፍቶ የቀዳሚ ምርመራ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለትናንት ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን ተጠርጣሪዎች ‘በተሰየሙት ዳኛ ገለልተኛነት ላይ እምነት የለንም’ በሚል አቤቱታ በማቅረባቸው አቤቱታው ለፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር እንዲቀርብ ትዕዛዝ መሰጠቱ ይታወሳል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top