Connect with us

ኢባትሎአድ በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ

ኢባትሎአድ በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

ኢባትሎአድ በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ

“የ2012 በጀት ዓመት በተለይ የአፈር ማዳበሪያና ስንዴን የማጓጓዝ ስራ በመሰራቱ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበትና ስኬታማ የሆንበት ዓመት ነው፡፡” የኢባትሎአድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጀት በ2012 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የዳቦ ስንዴ እና የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ አገልግሎት ሃላፊነቱን ወስዶ ወደ ስራ በመግባትና 46 መርከቦችን በማሰማራት 2.45 ሚሊዮን ቶን /24ሚሊዮን ኩንታል/ በላይ የዳቦ ስንዴና የአፈር ማዳበሪያን ማጓጓዙንና በስኬት ማጠናቀቁን የኢባትሎአድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በሁሉም አይነት የድርጅቱ አገልግሎቶች ማለትም በባሕር ትራንስፖርት፣ በደረቅ ወደብ፣ በየብስ ትራንስፖርት፣ እንዲሁም በመልቲሞዳል የኦፕሬሽን ስራዎች አገልግሎት አጠቃላይ 11 ሚሊዮን ቶን ገቢ እና ወጪ ጭነት ማስተናገድ ተችሏል፡፡

ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ከተስተናገደው 7 ሚሊዮን ቶን ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበና የ37 በመቶ ጭማሪ ያሳየ መሆኑን አቶ ሮባ ተናግረዋል፡፡

ሌላው በበጀት ዓመቱ በከፍተኛ ስኬት የሚገለጸው ከዚህ በፊት ከ700 ሺ ቶን ያልበለጠ ጭነት የሚሰሩት የድርጅቱ መርከቦች ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት ማጓጓዝ መቻላቸውንና ከዕቅዱ አንፃር ሲታይ አፈፃፀሙም ከፍተኛ መሆኑን ነው አቶ ሮባ የገለጹት፡፡

በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ከታክስ በፊት 2.56 ቢሊዮን በላይ ብር ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 104% ማሳካት ችሏል፡፡

በሌላ በኩል የወጪ ንግድን (ኤክስፖርት) ከማበረታታት አንፃር ድርጅታችን ልዩ ልዩ ድጋፎችን ያደርጋል ያሉት አቶ ሮባ በዚህም ለደንበኞች በተደረገ የየብስና የባህር የአገልግሎት ክፍያ ቅናሽ የ17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል፡፡

#ኢባትሎአድ

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top