Connect with us

በኦሮሚያ ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ

በኦሮሚያ ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ
People walk past a poster of slain Ethiopian singer Hachalu Hundessa whose death sparked the worst bout of unrest since Prime Minister Abiy Ahmed took charge in 2018. (Dawit Endeshaw/REUTERS)

ወንጀል ነክ

በኦሮሚያ ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ

በኦሮሚያ ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ታሰሩ
~ ቀሪዎቹ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ናቸው፣

በኦሮሚያ ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከ1 ሺህ 700 በላይ የዞንና የወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በኦሮሚያ ክልል ባሳለፍነው ወር ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ እርምጃው የተወሰደው ከመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባልቻሉ እና በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ውስጥ ተሳትፈዋል በተባሉ ሰራተኞች ላይ ነው።

በዚህም መሰረት እርምጃው ከ500 በላይ በመሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ በሚሆኑ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ላይ መወሰዱን ቢሮው አስታውቋል።

በክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ የህግ እና የፖለቲካ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ቢሮው በመግለጫው አክሎም፥ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት ከ500 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው ኮንፍረንስ መወሰኑንም ቢሮው በመግለጫው አስታውሷል።

#FBC

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top