Connect with us

አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ

አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸውን የሚመለከት ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ

በወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ግለሰቦች ጉዳያቸውን የሚመለከት ዳኛ እንዲቀየር አቤቱታ አቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት ባለ ሰባት ገጽ አቤቱታ ጉዳዩን እየተመለከቱት ያሉት ዳኛ ገለልተኛ ናቸው ብለው እንደማያምኑ በመግለጽ ዳኛው እንዲነሱ ጠይቀዋል።

በወንጀል ጉዳይ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 የተለያዩ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ልደታ አዳራሽ ታይቷል።

ችሎቱ የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት የተሰየመ ቢሆንም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ባቀረቡት አቤቱታ “ችሎቱን የሚመለከቱት ዳኛ ገለልተኛ ሆነው ጉዳያችንን ሊመለከቱ ስለማይችሉ ይነሱልን” ሲሉ አመልክተዋል።

ጉዳዩን የመረመሩት ዳኛ በበኩላቸው “ከጉዳዩ መነሳት የለብኝም” የሚል ሐሳብ አቅርበው በሰጡት ትዕዛዝ ጉዳዩ ለፍርድ ቤቱ ሬጅስትራል እንዲቀርብ አዘዋል።

ጉዳዩ በሬጅስትራሩ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ተጠርጣሪዎች በማረሚያ እንዲቆዩ በመወሰን መዝገቡ መዘጋቱን አሳውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top