Connect with us

የከንቲባው ንብረት የኾነችው አዲስ አበባ

የከንቲባው ንብረት የኾነችው አዲስ አበባ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የከንቲባው ንብረት የኾነችው አዲስ አበባ

የቀጠለው የኣዲስ ኣበባ የመሬት ወረራና የከንቲባው ንብረት የኾነችው ኣዲስ ኣበባ

(ከሰሎሞን ኃይለ)
የአዲስ አበባ ጉዳይ ውሎ ሲያድር በሚጋለጥ ብዙ ምስጢራት የተሞላ ነው፡፡ በከተማዋ ዳርቻዎች ህጋዊ ሽፋን ያላቸው መሬት ወራሪዎች የከተማውን መሬት ሸንሽኖ አከፋፋይ መሃንዲሶች ሆነዋል፡፡

ከተማዋ የሜትሮፖሊቲያን ቅርጽዋን ኣጥታ የኣንድ ሰው ንብረት መስላለች፡፡ ምክትል ከንቲባና ካቢኔ ያላት ኣትመስልም፡፡ ኣንዷ ከንቲባዋ እዚህም እዚያም ይታያሉ፡፡ ቤት ይሰጣሉ፤ ገንዘብ ይሰጣሉ፤ ችግር ይፈታሉ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ ኣሁን በኣቶ ኣብዲ ኢሌ መንገድ እየሄዱ ይመስላሉ፡፡ እኒያ ብር አዳዮ ሲባሉ እኒህ ደግሞ መሬት ኣዳይ በሚለው ሀሜት ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከንቲባው እንደ ጃነሆይ ናቸው፡፡ ስዕል አይተው ከወደዱት ከመንግስት ካዝና ሰዓሊውን ይሸልማሉ፡፡ ግጥም ቀርቦ ካረካቸው ገጣሚውን ቢያንስ ሳይክል ከመቀበል የሚያግደው ኣይኖርም፡፡ ከኪስም ባይሆን መስጠት በራሱ ደግ ነው፡፡ ግን ስጦታዎች ሁሉ ህግን ተከትለዋል ወይ? የሚለው የሚመለሰው እሳቸውም የጄነራል ክንፈን ኣይነት እጣ ፈንታ ሲገጥማቸው የሚረጋገጥ ነው፡፡

የመሬት ደላሎቹ ሩጫ፣ የኣንድ ፍሬ ልጆች ባለ ብዙ መቶ ሺህ ብሮች ባለቤትነት፣ የመሬት ንግዱ ያመጣው ገቢና ሆሆይታ ግን የደህንነቱን መዋቅር ኣንዳች ነገር ይጠቁሙታል ብዬ ኣስባለሁ፡፡

መሬት በህገ ወጥ መልኩ እየታደለ መሆኑን ለማየት መሬት መግዛት እፈልጋለሁ ብሎ ለደላላ መንገር በቂ ነው፡፡ ምላሹ ያስደነግጣል ኣዲስ ኣበባ እንደ ተራ ሸቀጥ ወጣቶች ለክተው የሚያከፋፍሏት መዲና ሆናለች፡፡

ተጠያቂነት የለም ሚሊዮን ብሮች ከተጠሩ ቆዮ፡፡ ቢሊዮን ብሮች በዝተዋል፤ ከዚህ ቀደም የነበረው መንግስት ቢሊዮን የጠራባቸው ፕሮጀክቶች ቢያንስ ግልገል ግቤ አንድና ሁለት፣ የጎተራ መንገድ፣ ጣና በለስ፣ ተከዜና ህዳሴው ግድብ ናቸው፡፡

ኣዲስ ኣበባ የማን ናት ብሎ መጠየቅ ኣሁን ሞኝነት ነው፡፡ ህዝቡ ራሱን በእዳ እንደተያዘ ንብረት ለምን ብሎ በማይጠይቅበት የተምታታ መንፈስ ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

በህወሃት ዘመን ያልተፈጸመ ወንጀል፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ወረራና የሀብት ብክነት ሲመለከት ለምን ሲል ህወሃት ልኮህ ነው ብለው ይነግሩታል፡፡ ወንጀልን መከላከል ለውጥ ማደናቀፍ ሆኖ ከተቆጠረ ቀን ጀምሮ አትንገሩኝ የሚል መዋቅር ከተማዋን የግሉ አድርጓታል፡፡

ኣዲስ ኣበባን እንደ ከንቲባው የግል ርስት ብንቆጥራት እንኳን የምክትሎቻቸው ድርሻ የቱ ጋር ነው፤ የምክር ቤቱ ድርሻ የቱ ጋር ነው? የነዋሪው ድርሻ የቱ ጋር ነው? ከተማዋ ብቻ ናት እኛም የከንቲባው ነን? ማነው ይኼን የሚነግረን፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top