Connect with us

ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት የፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን ተያዙ

ፌዴራል ፖሊስ

ህግና ስርዓት

ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት የፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን ተያዙ

ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት የፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ።

ባለፈው ሳምንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ መስጅድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለና በምርመራ ሂደት ላይ ያለ በብዙ ሚሊየን ብር የሚገመት የፌሮ ብረት “ህጋዊነቱ ስለተረጋገጠ በቦታው የሚገኘው የፖሊስ ጥበቃ ተነስቶላቸው ወደ ፈለጉበት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅደናል” የሚል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተፃፈ በማስመሰል ሀሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅተው በመያዝና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ ባንክ አስገብተውና በቼክ አዘጋጅተው ብረቱን በአምስት ተሽከርካሪ ጭነው ሊወጡ ሲሉ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፋይናንስ ኢንተለጀንስ ጠንካራ ክትትል ሊያዙ ችለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት፦

1. አቶ ደመላሽ አድማስ ታምር
2. አቶ እምሩ ከበደ ሀጎስ ወይም ሀብቶም
3. ወ/ሮ ዳግማዊት መስፍን

የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት የተያዘው ብረት ባለቤት ነኝ ከሚል፣ አቶ ተክላይ ከሚባልና አሜሪካን ሀገር ነዋሪ ከሆነ ግለሰብ ጋር ሶስቱ ተጠርጣሪዎች የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኤግዚቢትነት ተይዞ በምርመራ ሂደት ላይ ያለውን የፌሮ ብረት በጥበቃ ላይ ላሉት የፖሊስ አባላትና አመራሮች 500 ሺህ ብር ጉቦ ለመስጠት በአቢሲኒያ ባንክ አዲስ አካውንት ከፈተው ያስገቡ መሆኑን፤ በተመሳሳይ ለሌሎች የፀጥታ አካላት 400 ሺህ ብር በባንክ እና የ25 ሚሊዮን ብር ቼክ አዘጋጅተው ብረቱ እንደሚለቀቅ ከተስማሙ በኋላ የፖሊስና የፀጥታ አካላቱ ጉዳዩን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ለበላይ ሃላፊ በማሳወቅ ሂደቱ እንዲቀጥል ካደረጉ በኋላ ብረቱን በአራት ሲኖትራክ እና በአንድ ክሬን ለመጫን ተስማምተው በሁለት ሲኖትራክ እንደተጫነ ባንክ የገባው ብር እና ቼኩ፣ እንዲሁም የተፃፈው ሀሰተኛ ደብዳቤ እና ሶስቱ ተጣርጣሪዎች በተጨማሪም፡-

1.ኮድ 3- 63911 ኢት ሲኖትራክ
2.ኮድ 3- 80559 ኢት ሲኖትራክ
3.ኮድ 3-67732 ኢት ሲኖትራክ
4.ኮድ 3-67617 ኢት ሲኖትራክ እና
5.ኮድ 3-53243 ኢት ክሬን ክራፍት ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

ብረቱ ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ በምርመራ ሂደት ላይ ያለ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ ለፀጥታ አካላት በርካታ ገንዘብ ሰጥተው በማማለል ለህገ- ወጥ ድርጊት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደረጉትን ጥረት በማክሸፍና ለህግና ለመንግስት ፍፁም ታማኝ በመሆን ወንጀሉ ለህግ እንዲቀርብ በማድረግ የጁንታውን እኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻላቸው ታውቋል፡፡

የፀጥታ ሀይሎቹ ለሙያ ስነ-ምግባር ተገዥ በመሆንና ለህዝብና ለመንግስት የገቡትን ቃል-ኪዳን በመጠበቅና በማክበር ለፈፀሙት ሙያዊ ተግባር ተቋሙ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ ህብረተሰቡ አሁንም በዚህ አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ለመሳተፍ የሚጥሩ ጁንታውና ከጁንታው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሀገራችን ላይ የሚያሴሩ ባንዳ ግለሰቦችን እየጠቆመ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡(አ/አ ኘረስ ሴክሬቴሪያት)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top