Connect with us

የዓለም የጤና ድርጅት በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚጠበቅበትን ማድረጉን ገለጸ

ከአስር ሰዎች አንዱ በኮሮና ቫይረስ ሊያዝ ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት
AFP via Getty

አለም አቀፍ

የዓለም የጤና ድርጅት በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚጠበቅበትን ማድረጉን ገለጸ

የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያባከነው ጊዜ አለመኖሩን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አርብ ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን በጥር ወር መጨረሻ ላይ ይፋ መደረጉን ጠቅሰው የተሰጠው ጊዜ በወረርሽኙ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ በቂ ነበር ብለዋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ወረርሽኙ የጤና ስጋት መሆኑን ሲያውጅ ከቻይና ውጪ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ብቻ የነበረ ሲሆኑ በወቅቱ የሞተ ሰውም አልነበረም ብለዋል፡፡ አሁንም በሽታው የዓለም ኅብረተሰብ ጤና ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመልክተዋል።

በተለይም ደካማ የጤና አገልግሎት ሥርዓት ባላቸው አገራት ውስጥ በሽታው እየጨመረ በመምጣቱ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

በሽታው ከተከሰተ በሶስት ወራት ውስጥ ከ3.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን 239 ሺህ 623 ሰዎች ደግሞ በመላው ዓለም ለሞት ተዳርገዋል።

ምንጭ:- ቢቢሲ

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top