Connect with us

ኮሮናቫይረስ፡ “ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው” ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ

ኮሮናቫይረስ፡ “ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው” ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ
Photo: Social Media

ጤና

ኮሮናቫይረስ፡ “ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው” ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ

ኮሮናቫይረስ፡ “ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው” ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ

በኦሮምኛ የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ ሳምንታት መቆጠሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።

ድምጻዊው “በሽታው እንዲህ አይነት ቦታ ያዘኝ ብዬ መናገር አልችልም” ካለ በኋላ የሚጠረጥረው ስፍራ እንዳለ ግን ገልጿል።

ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ በተገደለበት እለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ ከጓደኞቹ ጋር በሆስፒታል ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ እንደነበር ያስታውሳል።

አምቦ በነበረው የቀብር ስነስርዓት ላይም አብዛኛው ሰው በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልተጠቀመም ነበር።

ትልቁ ጥርጣሬዬ ይህ እንደሆነ የሚናገረው ድምጻዊ ሂቲቃ፣ ከአምቦ ከተመለሰ በኋላ የሕመም ስሜት ተሰምቶት ወደ ግል ጤና ጣብያ ቢሄድም ሌላ በሽታ ነው ተብሎ መርፌና ኪኒን ታዘዘለት።

ይሁን እንጂ በራሱ ላይ የተመለከታቸው የሕመም ስሜቶች የኮሮናቫይረስ ነበሩ ይላል ድምጻዊ ሂቲቃ።

” ሰውነቴ በጣም ይደክማል፤ ደረቅ ሳል ሳያቋርጥ ለሶስት ሰዓት ያስለኝ ነበር” በማለት ከዚያ በኋላ ለጤና ቢሮ በመደወል ምርመራ እንደተደረገለት እና በኮሮናቫይረስ መያዙ ሲረጋገጥም ወደ ሚሌኒየም አዳራሽ ተወስዶ ሕክምና እና እንክብካቤ ሲደረግለት መቆየቱን ይናገራል።

“የምኖረው ከእህቴ ጋር ነው፣ እርሷም ተይዛ ነበር፤ እርሷ ህመም እንደኔ ስላልጠናባት ቤት ውስጥ በተደረገላት እንክብካቤ ነው የተሻላት፤ እኔ ግን ለሁለት ሳምንታት ሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ ሕክምና ድጋፍ ተደርጎልኛል።” ይላል

በሚሊኒየም አዳራሽ ያሳለፋቸው ሁለት ሳምንታት ፈታኝ እንደነበረ የሚናገረው ኢቲቃ ሆኖም በጤና ባለሙያዎቹ ለታማሚዎች የሚደረገው ህክምናና እንክብካቤ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ይጠቅሳል።

በከባድ ህመም ያሳለፈባቸው ሳምንታት በመጥቀስ ማህበረሰቡ በሽታውን አቅልሎ ማየት እንደሌለበትም ይመክራል።

” ሳሉ በጣም ከባድ ነበር፤ ሁለት ለሊት ጭንቅላቴን ይዤ ነበር ሳስል ያሳለፍኩት፤ ከሚነገረው በላይ በጣም በጣም ከባድ ጊዜ ነበር፤ ስለበሽታው ሲናገሩት እና ታመው ሲያዩት በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ስለዚህ ለራስ ጥንቃቄ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው።” በማለት መልእክቱን አስተላልፏል።

ድምጻዊ ሂቲቃ፣ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ የዳነ ባይሆንም ከአምስት ቀናት በፊት ከሚሌኒየም የማቆያና ህክምና ማእከል በመውጣት ወደ ቤቱ ተመልሷል።

“ቤት እየተመላለስን እንከታተልሃለን ተብዬ ነው የወጣሁት” በማለት የጤና ባለሙያዎቹ ቃል በገቡት መሰረት ከማቆያው ከተመለሰ በኋላ ቤቱ ድረስ እየመጡ ክትትል እንዳደረጉለት ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሞልቶ ባይሻለውም ከነበረበት ሁኔታ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

“በህመሜ ሰዓት በሁሉም መንገድ ይጠይቁኝና ሲያበራቱኝ የነበሩ አድናቂዎቼና ማህበረሰቡን ላመሰግን እወዳለሁ፤ አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ፤ ከሚያሰጋኝ ነገር ውስጥ ወጥቻለሁ ማለት እችላለሁ።”(BBC)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top