Connect with us

ለድህረ ኮሮና የቱሪዝም ልማት የባተለው ቱሪዝም ኢትዮጵያ

ለድህረ ኮሮና የቱሪዝም ልማት የባተለው ቱሪዝም ኢትዮጵያ

መዝናኛ

ለድህረ ኮሮና የቱሪዝም ልማት የባተለው ቱሪዝም ኢትዮጵያ

ለድህረ ኮሮና የቱሪዝም ልማት የባተለው ቱሪዝም ኢትዮጵያ፤ ሀገራችን የጉብኝት ደህንነት ማረጋገጫ እንድትቀበል አድርጓል
(ሄኖክ ስዩም ~ድሬቲዩብ)

የዓለም ጉዞና ቱሪዝም ምክር ቤት ለኢትዮጵያ የጉዞ ደህነት ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ ቱሪዝም ኢትዮጵያ በኮሮናው ዘመን የሰራቸው በርካታ ስራዎች በቱሪዝም መዳረሻዎችና በቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አካባቢ ፈታኙን ዘመን ለማለፍ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን ያለ እረፍት ሰርቶ ነበር፡፡

ለድህረ ኮሮና የቱሪዝም ልማት የባተለው ቱሪዝም ኢትዮጵያ

የዓለም ጉዞና ቱሪዝም ምክር ቤት ለኢትዮጵያ የጉዞ ደህነት ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ 

የመዳረሻ አካባቢዎች ዓለም አቀፉን የኮቪድ 19 ወረርሺኝ መከላከል በሚቻልበት የቱሪዝም ፕሮቶኮል እንዲሰሩ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ዋና ዋና መዳረሻዎችን ጸረ ተህዋስ ጭምር የመርጨት፣ ወረርሺኙን በሚቆጣጠር አግባብ መዳረሻዎችን ለመክፈት የሚያስችሉ ተከታታይ ስልጠናዎችን የመስጠትና ሀገራችን ራሱን ቢቀጥልም ቢቆምም ከዓለም ጋር ኮቪድ 19 ሳንካ ሳይሆን የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በምትቀላቀልበት ስልት ላይ ብዙ ደክሟል፡፡ የድካሙን ፍሬም ተቀብሏል፡፡ ሀገርን ወክሎ የኢትዮጵያን የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ ተቀብሏል፡፡

የጉዞና ጉብኝት ማረጋገጫውን የደህንነት ማህተም በክብር ከወሰዱት አስራ ሦስት የአፍሪቃ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ደቡብ አፍሪቃ መንገድ ላይ ስትሆን ግብጽና ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር መውሰዳቸው በአንድ አውድ የጉብኝት መስመር ለተካተተው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቀጠና ፋይዳው ከፍተኛ ነው፡፡

ዘጠኝ የሚሆኑት የአውሮፓ ሀገራትም ተመሳሳይ የደህንነቱ ማህተም ባለቤቶች ሆነዋል፡፡ ኦስትሪያ ሩሲያ ስፔንና ዩኬ ደግሞ በር ላይ ናቸው፡፡ ጆርዳን፣ ሳውዲ፣ ካዛኪስታንና፣ ኡዝቤኪስታን ከመካከለኛው ምስራቅ የደህንነት ማረጋገጫውን ወስደዋል፡፡
ከአህጉራቱ በርከት ያሉ ሀገራት ለዚሁ የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ ማህተም የታደሉት የደቡብ አሜሪካ ቀጠና ሀገራት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ አስቀድማ የደከመችበት የኮቪድ መከላከል የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ፕሮቶኮል በተጠናከረ መልኩ በመተግበር ከቀጠለችና አሁን የሚታየውን የመከላከል መፋዘዝ ከቀረፈች ከዓለም ዘንድ ካገኘችው ተመዝኖ ለብቃት የመድረስ የጉብኚ ደህንነት ማረጋገጫ ማህተም ጋር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል እምነታችን ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ያለ እረፍት በሰራው ስራ ሀገር የሚጠቅም ስኬት አስመዝግቧልና ሊመሰገን ይገባል፡፡

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top