Connect with us

የጆ ባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ

የጆ ባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ
FBC

አለም አቀፍ

የጆ ባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ

የጆ ባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚመራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ

 

 በእጅጉ ሲጠበቅ የነበረውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ማሸነፋቸው እውን ሆኗል።

ፕሬዚዳንቱ በይፋ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናን እስከሚረከቡ ድረስ የሽግግር ቡድን አዋቅረዋል።

ይህ ቡድን የጆ ባይደን አስተዳደር በቀጣይ አሜሪካን የሚመራባቸው የአስተዳደር መሰረተ ልማቶችን የማዋቀር ስራ ያከናውናል።

በመሆኑም የሽግግር ቡድኑ አሜሪካ ያጋጠማትን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የኢኮኖሚ ውድቀት እንዴት መወጣት እንደምትችል አሰራሮችን ይዘረጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

እንዲሁም በአጠቃላይ የመንግስትን ቀጣይነት የማረጋገጥ ስራም እንደሚያከናውን ነው የተነገረው።

በዚህ ቡድን ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች መካከል ኢትዮ አሜሪካዊው ዮሐንስ አብርሃም አንዱ ነው።

ዮሐንስ አብርሃም የባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት ስራ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጠው ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ የቅርብ ሰው መሆኑም ይነገራል። 

ዮሐንስ በባራክ ሁሴን ኦባማ አስተዳደር ለስምንት ዓመታት በነጩ ቤተ መንግስት ሰርቷል። 

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቹ ቨርጂንያ ስፕሪንግፊልድ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ዮሐንስ ሃርቫርድ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በህግ መምህርነት አገልግሏል።

ይህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በጆ ባይደን አስተዳደር ከፍ ያለ ቦታ መያዙ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተነግሯል።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ኤፍ.ቢ.ሲ

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top