Connect with us

ፖሊስ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመርኩኝ አለ

ፖሊስ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመርኩኝ አለ
Photo: ethiopian reporter

ህግና ስርዓት

ፖሊስ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመርኩኝ አለ

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ ከዛሬ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭ ጋር በተያያዘ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ዜጎች ሐሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ያወጣቸውን ሕጎች እና ክልከላዎችን ሁሉ ሕዝቡ ተቀብሎ ተግባር ላይ እንዲያውለውም ጠይቀዋል።

ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ፣ አለመጨባበጥ እና እጅን አዘውትሮ መታጠብን የመሳሰሉ ኮሮናን ለመከላከል የወጡ ክልከላዎችን በሚተላለፉ አካላት ላይም ፌዴራል ፖሊስ አስተማሪ እርምጃ መወሰድ እንደሚጀምርም ነው ያስታወቁት።

የፌዴራል ፖሊስ በዚህ በሽታ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢታወጅም ሕጉን ለማስተግበር እና ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚሄዱ ጉዳዮችን ለመተግበር ዝግጅቱ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ሕገ-ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ 5 ሺህ የሚደርሱ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና እርምጃው በሌሎች መሰል ነጋዴዎች እንደሚወሰድም ተናግረዋል።

የምሽት ጭፈራ ቤቶች እና ክልከላ የተደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ክልከላውን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ አላደረጉም ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ፌዴራል ፖሊስ የክልከላዎቹን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ያወጣቸውን ሕጎች እና ክልከላዎችን ሁሉ ሕዝቡ ተቀብሎ ተግባር ላይ እንዲያውለውም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።(ኢኘድ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top