Connect with us

የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት በኢትዮጵያ ሀገር በቀልና ዘመናዊ ሳይንስን በማጣመር

የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት በኢትዮጵያ ሀገር በቀልና ዘመናዊ ሳይንስን በማጣመር
Photo Facebook

ዜና

የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት በኢትዮጵያ ሀገር በቀልና ዘመናዊ ሳይንስን በማጣመር

የኮሮና ቫይረስ መድኃኒት በኢትዮጵያ ሀገር በቀልና ዘመናዊ ሳይንስን በማጣመር ለማግኘት ውጤታማ ሂደት ላይ መሆኑን የቴክኖሎጂ ኢኖቬሽም ሚኒስትር አስታወቀ፡፡

የሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት የኮሮና ቫይረስን ለማከም የተሠራው መድኃኒት መሠረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት ማለፉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ መሆኑን ያስታወቀው ሚኒስሩ ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ሥራዎች እንዲሸጋገር መደረጉን ነው በማኅበራዊ ገጹ ያስታወቀው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶክተር፣ ኢንጂነር)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶክተር) ከኢትዮጵያውያን የባህል ሐኪሞች ጋር እና የሕክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሕክምና የተዘጋጀውን መድኃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

መድኃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡
የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው፤ ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተም ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡

መድኃኒቱ ገና በምርምር ሂደት ላይ ያለመሆኑን በመረዳት ከጥንቃቄ መዘናጋት ግን አይገባም፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top