Connect with us

የአርባ ሰባት ዓመታት ትዝታ የቀሰቀሰው ቀለበት

የአርባ ሰባት ዓመታት ትዝታ የቀሰቀሰው ቀለበት
Photo: Facebook

አስገራሚ

የአርባ ሰባት ዓመታት ትዝታ የቀሰቀሰው ቀለበት

ብዙ ጊዜ ጌጣጌጦች ጠፉ ሲባል ቢሰማም ፈልጎ የማግኘቱ ጉዳይ እንደ መግዛቱ ቀላል አይሆንም። በተለይ የወርቅ ጌጣ ጌጥ ጠፍቶ የመገኘት እድሉ ጠባብ ነው።ወርቅ ውድና ተፈላጊ እንደመሆኑ ያገኘውም ሰው ቢሆን የጠፋበትን ባለቤቱን አፈላልጎ ይሰጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።ሊገኝ የሚችልበት እድል አንድና አንድ ብቻ ነው። ሰው እጅ ያልገባ ከሆነ ብቻ።ይህ ሲሆን ከእለታት አንድ ቀን ሊገኝ ይችል ይሆናል።

የጌጣጌጦች መጠን አነስተኛ መሆን ከሚጠፉበት ቦታ ውስብስብነት ጋር ተዳምሮ የመገኘት እድላቸውንም በእጅጉ ያጠበዋል። በዚህም የጠፉት ጌጣጌጦች ከናካቴው ተሰውረው ሊቀሩ አልያም ጥቂት ጊዜ ፈጅተው ባጋጣሚ ሊገኙ ይችላሉ ።ጌጣጌጦች ከጠፉ ረጅም አመታትን አስቆጥረው ሲገኙ ግን ግርምትን ያጭራሉ። ስካይ ኒውስ ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ ይዞት ብቅ ያለው መረጃም ይህንኑ ሃቅ ያረጋግጣል።

በ1973 ገና አፍላ ወጣት የነበረችው ዴብራ ሜኬና ብረንስዊክ ሜይን በተሰኘችው የአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተማ በሚገኝ አንድ የእቃ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ ባሏ ያደረገላትን ቀለበት ትጥላለች። ቀለበቱ ከጠፋ ከአርባ ሰባት አመታት በኋላም በቅርቡ በአንድ የብረት ሰራተኛ በፊንላንድ ደን ውስጥ ተቀብሮ ተገኝቷል።

ሜኬና በአሁኑ ወቅት 63 ዓመቷ ሲሆን፣ በሞርስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለች በፖርትላንድ ውስጥ ቀለበቱ እንደጠፋባት ባንጎር የተሰኘው ጋዜጣ በወቅቱ ዘግቦ እንደነበር ድረገጹ አስነብቧል።

BRUNSWICK, MAINE — 02/13/20 — Shawn Mckenna’s 1973 Morse High School class recently turned up buried in forest in Finland. The man who found it mailed it to Mckenna’s widow in Brunswick. Troy R. Bennett | BDN

ትምህርት ቤቱን የሚለይ ምልክት ያለበት ይኼው ቀለበት የቀድሞ የሜኬን ባል በትምህርት ቤትና በኮሌጅ ተገናኝተው ሲያወሩ ያበረከተላት እንደነበር ታውቋል።

ባለቤቷ ሻውን ለስድስት አመታት ያህል ከያዘው የካንሰር ህመም ጋር ሲታገል ቆይቶ በ2017 ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ባልና ሚስቶቹ ለአርባ አመታት ያህል በትዳር መቆየታቸውም ተጠቅሷል።

ሸዋን የኮሌጅ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ቀለበቱን ለሜኬን የሰጣት ሲሆን፣ ሆኖም መጋዘን ውስጥ በድንገት እንደጣለችው አስታውሳለች። የብረት ሰራተኛው ቀለበቱን ከተቀበረበት እስካገኘበት ጊዜ ድረስ ተረስቶ እንደነበርም ገልፃለች።

የብረት ሰራተኛው ሰማያዊ ፈር ያለውን ብራማ ቀለበት ሲያገኝ የብረት መመርመሪያ ተጠቅሟል፤ ብዙ ጊዜ ያገኝ የነበረው ግን የብረት ኩባያ ወይም ቁራጭ ብረት እንደነበረም የፊንላንድ ሚዲያ ዘግቧል። በቀለበቱ ላይ የተፃፈውን የትምህርት ቤት ምልክትና የምርቃ አመተ ምህረት በመያዝ አልሙኒ ከተሰኘ ማህበር ጋር እንደተገናኘም ሚዲያው ጠቅሷል።

በዚሁ መሰረት መኬን ከረጅም አመታት በፊት የጠፋባት ቀለበት እንደተገኘና መውሰድ እንደምትችል በስልክ ሲነገራት እምባ እንደተናነቃትና የወጣትነት የፍቅር ጊዜዋን እንዳስታወሳት ገልፃለች። ‹‹ቀናነት በጎደለበት በዚህ ዘመን እንደዚህ አይነት ሰዎችን ማግኘት በጣም ይከብዳል›› ስትልም ተደምጣለች። ‹‹በአለማችን ጥሩ ሰዎች አሉ፤ ስለዚህ ተጨማሪ ጥሩ ሰዎችን እንፈልጋለንም›› ብላለች።

ሜኬና ከጠፋ ረጅም አመታትን ያስቆጠረው ቀለበት እንዴት በፊንላንድ ደን ውስጥ ሊገኝ እንደቻለ ምንም የምታውቀው ምክንያት እንደሌለ አስታውቃለች። ምን አልባት ባለቤቷ ሹዋን በ1990ዎቹ አካባቢ አብዛኛውን ጊዜውን በፊንላንድ ያሳልፍ በነበረበት ወቅት እሱን ብላ ስትሄድ ቀለበቱ አካባቢው ላይ ሳይጠፋ እንዳልቀረ ጠቅሳለች።

አዲስ ዘመን የካቲት 17/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top