Connect with us

ሰሜን ኮሪያ በኮሮና ቪረስ እንደተያዘ የጠረጠረችውን ግለሰብ መግደሏ አነጋጋሪ ሆኗል

ሰሜን ኮሪያ በኮሮና ቪረስ እንደተያዘ የጠረጠረችውን ግለሰብ መግደሏ አነጋጋሪ ሆኗል!
Photo: Facebook

አስገራሚ

ሰሜን ኮሪያ በኮሮና ቪረስ እንደተያዘ የጠረጠረችውን ግለሰብ መግደሏ አነጋጋሪ ሆኗል

ከቻይና በቅርቡ ወደ አገሩ የተመለሰንና የአገሪቱ የንግድ ዘርፍ ላይ በሃላፊነት እንደሚሰራ የተነገረለት ግለሰቡ ቅርብ የጤና ክትትል እየተደረገለት ባለበት ሁኔታ የህዝብ መጠቀሚያ በሆነው የመታጠቢያ ስፍራ ላይ በመገኘቱ ሰሜን ኮሪያ በሞት ቀጥታዋለች ሲል ዴይሊ ሜል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የንግድ ባለሙያው የተላለፈበትን እገዳ ጥሶ ከተገኘ በኋላ የታሰረ ሲሆን ወዲያውም በመሳሪያ ተመቶ እንዲሞት ሆኗል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስን በሚመለከት በተጠርጣሪዎች ላይና ከቻይና ወደ አገሯ በሚገቡ ሰዎች ላይ የጦር ሃይሏን በመጠቀም ጭምር ተከታታይነት ያለው ምርመራን ታካሂዳለች፡፡እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የተጠቃ ሰዉ በምድሯ ላይ ባይገኝም እጅግ ለፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት የምርመራ ሂደትን ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች፡፡

ግለሰቡ የጦር ሃይሉን ህግ በመተላለፍና ባልተፈቀደለት ቦታ በመገኘቱ እርምጃው ተወስዶበታል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈ የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ቤተሰብና የደህንነት ኤጀጀንሲው አባል እንደሆነ የተነገረለት ሌላም ግለሰብ ወደ ቻይና ያደረገውን ጉዞ እንዳይታወቅበት አድርጓል በሚል ለብቻው ተገልሎ እንዲቆይ ተወስኖበታ፡፡

ቫይረሱ ከተስፋፋበት አገር ቆይታ የነበራቸው ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውንና አለመጠቃታቸውን ለማረጋገጥ የአለም የጠና ድርጅት ካስቀመጠው የ14 ቀን የጊዜ ገደብ በላይ ሰሜን ኮሪያ 30 ቀናትን እየተጠቀመች እንደምትገኝ መረጃው አመላክቷል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በአሁኑ ሰዓት ብቸኛ የኢኮኖሚ አጋሯ ከሆነችው ቻይና ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የቫይረሱን ስርጭት በመስጋት ዝግ አድርጋለች፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top