Connect with us

“በሌላው ቤት መፍረስ የራስ ቤት አይገነባም”

"በሌላው ቤት መፍረስ የራስ ቤት አይገነባም"

ፓለቲካ

“በሌላው ቤት መፍረስ የራስ ቤት አይገነባም”

በሌላው ቤት መፍረስ የራስ ቤት አይገነባም” | በየሺሀሳብ አበራ

በኦዴፓ መካከል የተነሳው የውስጥ ስንጥቅ የኦሮሚያ ከተሞችን በሰልፍ አጨናንቋል፡፡ የኦሮሞ ወገኖቻችንም እየተማረሩ ነው፡፡ ሰልፉ በፀረ መደመር እና በተደማሪው፣በኮንፌዴራላዊዉ እና በተዋኻጁ መካከል ያለ ተቃርኖ ነው፡፡

ሶማሌ እና ደቡብ ህዝቦች ወደ አዲስ አበባ የሚያገናኛቸው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል፡፡ ኢህአዴግ በሁኔታው ቶሎ ካልወሰነ አዲስ አበባ እንደ ባግዳድ፣ኦሮሚያም እንደ ሶሪያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሁኔታውን ተንትኖ ለመፍትሄ መዘጋጀት እንጂ መበሻሸቅ አያስፈልግም፡፡

በሰው ችግር እና ስህተት እኛን ትክክል ከማድረግ በራሳችን መፍትሄ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ስክነት ፣መርህ፣ ነገ ከዚህ በላይ ቢመጣ እንዴት መፍትሄ ይሰራል የሚለውን ማሰብ እንጂ በቃላት ውርወራ ብቻ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ የዛሬው ግርግር መንግስታዊ እንጂ የአንድ ግለሰብ አይደለም፡፡ የመንግሥት ቢሆን ኑሮ ቢያንስ ቤተመንግስት እና አካባቢውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ግጭቱ ደግሞ የእርስ በእርስ በመሆኑ ለመደገፉም ሆነ ለመንቀፍ ያስቸግራል፡፡ ዋናው የራስን ቤት ማፅናት ነው፡፡ በሌላው ቤት መፍረስ የራስ ቤት አይገነባም፡፡

ባለፈው የዶክተር አብይ ደጋፊዎች በሽልማቱ ስም ተለልፈው ነበር፡፡ የዛሬኛው በጃዋር ስም ነው፡፡ ዓላማው ኦዴፓ ኒዮ ጎበና ዳጨ ነው የሚል ነው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ በሸዋ የበላይነት ወድቆ ወደ ማዕከላዊ መንግስቱ መቅረቡ ለፅንፈኛው ምቾት አይሰጥም፡፡ ለዚህም ይመስላል ዶክተር አብይ ጎበና ዳጨ ነው፣ነፍጠኛ ነው የሚሉት፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top