Connect with us

የተፈጸመብንን ግፍ የትግራይ ሕዝብ መጥቶ ይይልን

Social media

ነፃ ሃሳብ

የተፈጸመብንን ግፍ የትግራይ ሕዝብ መጥቶ ይይልን

የተፈጸመብንን ግፍ የትግራይ ሕዝብ መጥቶ ይይልን
~ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ
(አሳዬ ደርቤ ለድሬ ቲዩብ)

አባታችንን ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ለሕዝባቸው ሟች፣ ለእውነት ተሟጋች ሆነው የተገኙት ዛሬ ሳይሆን ያኔ የህውሓት ሥርዓት ሥልጣን ላይ ሳለ ነበር፡፡

እናም እንቢተኛ ወጣቶች በየስፍራው በሚያነሱት ተቃውሞ መፍረክረክ የጀመረው የማፊያ ቡድን በዓውዳመቱ ምድር ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጽ ወልዲያ ከተማ ላይ ያጋጥመዋል፡፡ ያን ጊዜም ወደ ስፍራው የተላከው የአጋዚ ወታደር በርካታ የወልድያ ከተማ ወጣቶችን ይጨፈጭፋል፡፡ አመጽና ቁጣውም ተባብሶ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በወቅቱም የሰሜን ወሎ ዞን ሊቀጳጳስ ረዳት—- የነበሩት ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ ወደ አደባባይ ወጥተው መከላከያ ሠራዊቱን በማውገዝ ለሐቅ ያላቸውን ታማኝነትና ለሕዝብ ያላቸውን ታማኝነት ያሳያሉ፡፡

‹‹የጸጥታ ሃይሎች ለምን እንደመጡ አናውቅም! ምናልባትም ሆን ብለው በዓሉን ለመረበሽና ወጣቱን ለመረሸን አስበው ሊሆን ይችላል የመጡት! እንዳጠቃላይ ግን ከእኛ አቅም በላይ የሆነው ምንም ያላጠፋው ወጣት ሳይሆን ልዩ ተልዕኮ አንግቦ ታቦት የተሸከመ ቄስ ላይ አስለቃሽ ጭስ ሊተኩስ የመጣው መከላከያ ሠራዊት ነው›› በማለት ያወግዛሉ፡፡ በዚህም የአባታችን ንግግር የተበሳጩት እነ ዳንኤል ብርሐነ ብጽዕነታቸውን ቀርቶ አንቱታውንም ነጥቀው ‹‹አንተ›› በሚል መጠሪያ ሲዘልፏቸው ነበር፡፡

ከወራት በፊት ደግሞ ከመንግሥትነት ወደ አሸባሪነት የተለወጠው ቡድን ወልዲያን ተቆጣጥሮ ዳግማዊ ዝርፊያውንና ጭፍጨፋውን ሲያካሄድ ብጽዕነታቸውን ያገኛቸው በዚያው ቅድስናቸው፣ በዚያው ንጽሕናቸው፣ በዚያው የሕዝብ ጠባቂነታቸው፣ በዚያው ጽናታቸው… ነበር፡፡

በእነዚያ ጊዜያትም አሸባሪው ሃይል ሲፈጽማቸው የነበሩ አረመኔያዊ ድርጊቶችን በውግዘታቸው ማስቆም ባይቻላቸውም ሕዝባቸው በርሐብ እንዳያልቅ፣ በፈተና እና በመከራ እንዳይራራቅ፣ ሥነ ልቦናው እንዳይደቅ፣ ማድረግ ችለዋል፡፡
የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች አባት በመሆን ፈንታ የሰው ልጆች አባት በመሆን ሙስሊም ክርስቲያን ሳይለዩ ሻል ካለው ሕዝብ የለመኑትን የእለት ጉርስ ጦም ላደረው ሲያርሱ ሰንብተዋል፡፡ ፖለቲከኞችና አመራሮች ጥለዋት በሄዷት ከተማ ውስጥ የሕዝብ መሪና የእርዳታ አስተባባሪ በመሆን እጅግ አስገራሚ ተግባራትን ተወጥተዋል፡፡

እራሳቸውን ለአደጋና ለጥቃት ዳርገው ክንፍ አልባ መላዕክ በመሆን የበርካቶችን ሞት አስቀርተዋል፡፡ በእኒህ አባት የቅድስና ጥግ የተገረመ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይም በእነዚያ ፈታኝ የመከራ ወራት የፈጸሙትን ገድል የሚገልጽ ቃል አጥቶ ‹‹የእኛ ቄስ›› እያለ ሲያወድሳቸው ነበር፡፡
ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገርመው ደግሞ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ወልዲያ ነጻ ከወጣች በኋላ በሚዲያ የተናገሩት ንግግር ነበር፡፡ ይሄንንም ቃለ-መጠይቃቸውን ስመለከት ያ ሁሉ ፈተናና መከራ በሰዋዊ ልባቸው ውስጥ አንዳች መጥፎ አሻራ ሳይጥል ማለፉ አስደናቂ ሆኖብኛል፡፡ ከአፋቸው የሚወጡትን ቃላት ሳዳምጥም ‹‹እኒህ አባት ግን እንደ እኛ ሰው ናቸው ወይ?›› ማለቴ አልቀረም፡፡

ምንም እንኳን አሸባሪው ሃይል ሕዝቡን ሲዘርፍና አገሩን ሲያራቁት የእሳቸውንም መኪና እንዳልማሩት ቢገልጹም ከዚያ በኋላ ግን ‹‹እውነት ግን እነዚህን ሰዎች የላካቸው የትግራይ ሕዝብ ነው?›› ብለው ከጠየቁ በኋላ ‹‹በፍጹም›› በማለት የእራሳቸውን ጥያቄ በእራሳቸው ይመልሳሉ፡፡ ከዚያም ወንጀለኞቹን ሕግ እንዲጠይቃቸው በማሳሰብ ፈንታ ወይም ደግሞ ‹‹እግዜር ይይላቸው›› ብለው በመራገም ፈንታ እንዲህ በሚል ቅዱሳዊ አስተሳሰብ ንግግራቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡

‹‹እነዚህ ሰዎች የፈጸሙብንን ተግባራት የትግራይ ሕዝብ መጥቶ ሊያይልን ይገባል››

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top