Connect with us

አቶ ሽመልስ በአክቲቪስት ጀዋርን አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

አቶ ሽመልስ በአክቲቪስት ጀዋርን አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አቶ ሽመልስ በአክቲቪስት ጀዋርን አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ትናንት ማታ የተፈጸመው ድርጊት ስህተት ነው፤ ስህተቱን ማን እንደፈጸመው፣ ለምን ጉዳዩን ምሽት ላይ ማድረግ እንደተፈለገ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡

•  ለሞቱት ወገኖች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

• በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡

• እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

• የተለያዩ አካላት ለውጡ ዘላቂነት እንዳይኖረው የተለያዩ ሙከራዎች ሲያደርጉ ነበር፡፡

• ዛሬ የተፈጸመው መሆን የሌለበት ነገር ነው፡፡

• መንግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ነው ለወንድማችን ጀዋርና ለሌሎች ከውጭ ለገቡ ሰዎች ጥበቃ የሚያደርገው፡፡

• አሳዛኝ ክስተቶች ዛሬ ተፈጽመዋል፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ድርጊቶቹን የፈጸሙ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፡፡

• በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ገንዘብ መድበው እየሰሩ ያሉ አካላት ስላሉ ህዝባችን ነቅቶ መንቀሳቀስ አለበት፡፡

• የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን ለማረጋጋት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ልትመሰገኑ ይገባል፡፡
• ህዝባችንን ተጠቃሚ የማያደርግ ማንኛውንም ተግባር አንፈጽምም፡፡

• ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እኩልነት ላይ የተመሰረተ እና ለሁላችንም የምትሆን የጋራ አገር በጋራ ለመገንባት መስራት አለብን፡፡

• በኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ብሔር ብሔረሰቦችን ለማቀፍና ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ የኦሮሚያ ቄሮዎችና ቀሬዎች መስራት አለባቸው፡፡

• አሁን ወንድማችን ጀዋር በሰላም ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፤ መንግስት የሚያደርግለት ጥበቃም ይቀጥላል፡፡

ምንጭ ኢቢሲ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top