Connect with us

ኦነግ ሸኔ 28 ንጹሀንን ሲገድል 12 አቁስሏል

ኦነግ ሸኔ 28 ንጹሀንን ሲገድል 12 አቁስሏል
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ወንጀል ነክ

ኦነግ ሸኔ 28 ንጹሀንን ሲገድል 12 አቁስሏል

ኦነግ ሸኔ 28 ንጹሀንን ሲገድል 12 አቁስሏል

– መንግስት በወሰደው የአጸፋ እርምጃ 3 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደምስሰዋል

ተስፋ የቆረጠው ኦነግ ሸኔ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈፅሟል ሲል የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ፤ በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ ትናትና ምሽት 3 ሰአት አካባቢ ነዋሪዎችን በግድ በማስወጣት በአንድ ቦታ ላይ በመያዝ በጦር መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል ብለዋል።

ይህም ቡድኑ የለየለት ሽብርተኛ መሆኑን አሳይቷል ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ።

በጥቃቱም  28 ሰዎች ሲሞቱ 12ቱ ቆስለዋል ያሉ ሲሆን ጥቃቱ የኦሮሞም የአማራም ተወላጆች ላይ መፈጸሙን ተናግረዋል።

ሁኔታው ከተከሰተ በኋላ ለማረጋጋት በስፍራው የደረሰው ሃይል በወሰደው እርምጃ 3 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው መደምሰሳቸውን እና ቀሪ ጥቃት ፈፃሚዎችን እና ርዝራዡን ለመያዝ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አጥፊ ቡድኑ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርስ እንደነበር የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ የህዝብ ቅራኔ ለመፍጠር ሲል የአማራ እና ሌሎች ብሄረሰቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል ብለዋል።

ፖሊስ ትእዛዝ አልተሰጠንም በሚል እርምጃ አልተወሰደም ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ሃሰት ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ ከዚህም ቀደም ተመሳሳይ ቅሬታዎች ቀርበው ሃሰት ሆነው መገኘታቸውን አብራርተዋል።

ነግር ግን በቀጣይ የማጣራት ስራ ተሰርቶ ትእዛዝ ደርሶት ያልፈፀመ ሃይል ካለ  ይጠየቃል ብለዋል።

ኦነግ ሸኔ የሁሉም ጠላት ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ፣ ከዚህ ቀደም በተወሰደ እርምጃ ከ2 ሺህ 600 በላይ ሃይሉን ያጣ በመሆኑና የህዋሓት መጨረሻም የታወቀ በመሆኑ ተስፋ ቆርጦ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደጀመረ ገልፀዋል።

የተጀመረው ለውጥ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ቢሆንም፤ ይህን ሀሳብ የማይቀበለውና የህዋሓትን ሃሳብ የሚያስፈፅመው ኦነግ ሸኔ ከዚህ ቀደም በርካታ የሰው ህይወት ነጥቋል ንብረትም አውድሟል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ሃይሉን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን የገለፁት ኮሚሽነር ጄኔራሉ በቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።(ኤፍ ቢሲ)

 

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top