Connect with us

በሁለቱ ክልል መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት አንድምታና ውጤት!

በሁለቱ ክልል መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት አንድምታና ውጤት!
ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

ዜና

በሁለቱ ክልል መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት አንድምታና ውጤት!

በሁለቱ ክልል መሪዎች መካከል የተካሄደው ውይይት አንድምታና ውጤት!

(ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

በምዕራብ ወለጋ ዞን የተካሄደውን አሰቃቂ ጅምላ ጭፍጨፋ ተከትሎ ሰሞኑን በኦሮሞያና በአማራ ክልል መሪዎች መካከል እዚህ አዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት በትንሹም ቢሆን ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፈና ውጤትም እያስገኘ የመጣ ይመስላል፣ እስካሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል፡፡

ለምሳሌ በነገሌ ቦረና የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ኦነግ-ሸኔዎችን እያሳደደ በመምታት ላይ መሆኑን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል፡፡ ይኸው የመረጃ ምንጭ በወለጋ አካባቢ ተመሳሳይ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንና በዚህም በርካቶች ተገድለው በርካቶች መማረካቸው ተረጋግጧል፣ በሌላ አነጋገር ከመቶ በላይ የኦነግ-ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውንና በአስሮች የሚቆጠሩ ደግሞ መያዛቸውን የመረጃ ምንጬ ገልጾልኛል፡፡

ቀደም ሲል ግን በፌዴራል ፖሊስም ሆነ በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ አዛዦች በኦነግ-ሸኔ ላይ ጨከን ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ስለማይፈልጉ ቁርጥ ሲሆን በቃ ተመለሱ ይሉ እንደነበር ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይም በዚህ ውይይት ላይ የአማራ ክልል አመራሮች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መረር ያለ ሀሳብና ጠንከር ያለ አቋም በመያዝ በሽመልስ አብዲሳ አጋፋሪነት የሚመራውን የኦሮሚያ አክራሪ ሀይል “በቃችሁ፣ እስካሁንም ቢሆን ለሀገር መቀጠል ብለን እንጂ ህዝባችን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በማን እየተደገፈ እንደሚከናወን እናውቃለን” የሚል አቋም ይዘው መቅረባቸው ታውቋል፡፡

በዚህም ምክንያት የፌዴራል መንግስቱም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ኦነግ-ሸኔ ላይ እንዲጨክኑ ተገደዋል፡፡ በመጨረሻም ቻግኒ ከተማ ውስጥ በደቦ ፍርድ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዝ ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ፣ ይኸ የመንጋ ፍርድ አንድም የአማራን ስነ ልቦና አይመጥንም፣ ሁለትም ሰበብ እየፈለጉ አማራን ለማስጨፍጨፍ ለሚነቀሳቀሱ ሴረኞች ዱላ የማቀበል ያህል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

ድርጊቱ ከሰብአዊነት አንጻር ከታየም ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ሌሎች ሲያደርጉት ትክክል እንዳልሆነ የምናወግዘውን ነገር እኛው ደጅ ሲመጣ ምክንያት መደርደር ተገቢ አይደለም፡፡ ስለሆነም የድርጊቱ ፈጻሚዎች በጥንቃቄ ተለይተው አስተማሪ የሆነ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top