Connect with us

ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሏል

ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሏል
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አርባ ዘጠኝ ማዞሪያና መቄዶኒያ አካባቢ እርምጃ ሲወሰድ

ወንጀል ነክ

ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሏል

ህገ ወጦች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጥሏል

 የመንገድ ግንባታ ስራ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይን ከሚጠያቁ የመሰረተ ልማት ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛውነው፡፡ ነገር ግን መንገድ ግንባታ ከፍተኛ ወጭ ተደርጎበት ቢገነባም በአጠቃቀምም ሆነ በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ምክንያቶች ለጉዳት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡

መንገዶች በዋናነት ሲገነባ ምቹና የተቀላጠፈ የትራፊክ አገልግሎት ለመስጠት ቢሆንም የመዲናችን ጎዳናዎች ግን ከታለመላው አላማ ውጭ የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሠጡ ይገኛሉ፡፡

ከነዚህም አገልግሎቶች መካከል የጋራዥና ጎሚስታ ስራዎችን ማከናወን፣ የመኪና እጥበት፣ የንግድ ስራዎች እና መንገድ ላይ የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን ማስቀመጥ ዋና ዋናወቹ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን  መንገዶች ዲዛይን የማድረግ፣ የመገንባት፣ የመጠገን እንዲሁም የማስተዳደር ስልጣንና ኃላፊነት አለው፡፡ መንገዶችን በመጠበቅና በመንባከብ ረገድም የመንገድ ሀብቱን ለማስተዳደር በሚያስችል መልኩ  የተደራጁና ክፍለ ከተዎችን ማእከል  ያደረጉ አምስት የመንገድ ሀብት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን አቋቁሞ እየሠራ ይገኛል፡፡

የምስራቅ አ/አ መንገድ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ ፅ/ቤቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለያዩ ቦታዎች በህገ ወጥ መልኩ መንገድ ላይ አሸዋና ጠጠር  ባከማቹ አካላት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡

ህግ በመተላለፍ የመንገድ መብት ጥሰት በፈፀሙ አካላት እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የፅሁፍ ማጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም እርምት ባለማድረጋቸው ምክንያት የተከማቸውን የግንባታ ግብአት ከመንገድ ሀብቱ ላይ የማንሳት ስራ ተሰርቷል፡፡

በመጨረሻም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ወጪ ተደርባቸው የሚገነቡ መንገዶችን ከጉዳት እንጠብቃቸው ፤ ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንጠቀማቸው  ሲል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡(አ/አ መንገዶች ባለስልጣን)

ፎቶ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አርባ ዘጠኝ ማዞሪያና መቄዶኒያ አካባቢ እርምጃ ሲወሰድ

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top