Connect with us

በአምስት ወራት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በአምስት ወራት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
ገቢዎች ሚ/ር

ወንጀል ነክ

በአምስት ወራት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በአምስት ወራት ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ባለፉት አምስት ወራት ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ/ም ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 118 ሺ ብር የሆነ የወጪና የገቢ ኮንትሮባንዶችን መቆጣጠር ተችሏል፡፡

ግምታዊ ዋጋቸው 981 ሚሊዬን 590 ሺህ የሚገመት የገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ 1ቢሊየን 100 ሚሊየን 631 ሺህ ብር የሚገመት ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ ተችሏል። ይህ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በተመሳሳይ 134 ሚሊየን 708 ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ታቅዶ 255 ሚሊየን 487 ሺህ  ዋጋ የሚያወጡ ወጪ ኮንትሮባንድ የተያዘ ሲሆን አፈፃፀሙ 190 በመቶ ነው፡፡ ይህ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 107 ሚሊዬን 276 ሺህ ብልጫ ሲኖረው የ72 በመቶ ጭማሪ፣ አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ በአምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው ብር 1 ቢሊየን 116 ሚሊየን 298 ሺህ የሆነ ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድን ለመያዝ ታቅዶ ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊየን 356 ሚሊየን 118ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ወጪና ገቢ ኮንትሮባንድ ለመያዝ ተችሏል፡፡ እነዚህ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለመያዝ ቀን እና ሌሊት በመስራት ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጉምሩክ ኬላ እና መቆጣጠርያ ጣቢያ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ ሀይሎችና ጥቆማ በመስጠት ለተባበሩ አካላት ሁሉ የገቢዎች ሚኒስቴር  ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ ወራትም ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ የገቢዎች  ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተጠናከረና የተቀናጀ ስራ ይሰራሉ፡፡(ገቢዎች ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top