Connect with us

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

ዜና

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በትግራይ ክልልና አጎራባች ከተሞች ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየሰራ ይገኛል፡፡

ተቋሙ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የመካከለኛና የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችን ለመጠገንና ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደነበረበት ለመመለስ ከትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተውጣጡ የቴክኒክ ባለሞያዎች በመላክ እስካሁን ሰፊ የጥገናና መልሶ ግንባታ ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ 

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከጎንደር ዲስትሪክትና ከዋናው ቢሮ ፕሮጀክት ክፍል የተውጣጡ ሁለት የቴክኒክ ቡድኖች ወደ ትግራይ ክልል በመላክ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና አጎራባች ከተሞች ለመመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የተሰማራው ግብረ ሃይል እስካሁን ወልቃይት፣ ሁመራ፣ ማይካድራ፣ አብድራፊ፣ አብረሃጅራ፣ ባዕከር፣ አዲረመጥና አዲጎሹ ከተሞች ላይ ያለው የዝቅተኛና መካከለኛ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል፡፡ 

ከበከር እስከ አዲረመፅ እና ከበከር እስከ ዳንሻ እንዲሁም ከማይፀብሪ እስከ አድርቃይ ያለው የመካከለኛና የዝቅተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ጥገናም ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ከሽሬ እስከ ማይፀብሪ ከተሞች ያለውን መስመር ጥገና ሥራም ለማከናወን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

በትግራይ ደቡባዊ አቅጣጫ ደግሞ ራያ ቆቦ፣ ጥሙጋ፣ ዋጃ፣ አላማጣ፣ ኮረም፣ ማይጫው፣ መሆኒ እንዲሁም ከአላማጣ ሰብስቴሽን ኃይል የሚያገኙትን ላሊበላና ሰቆጣ ከተሞች ላይ የደረሰውን ጉዳት ጠገኖ በአሁን ወቅት ሙሉ ለሙሉ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

በትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋቋመው የቴክኒክ ባለሞያዎች ቡድን ደግሞ የመቀሌ ከተማን ጨምሮ በኲዊሀ እና በአዲጉዶም ከተሞች ያለውን የዝቅተኛና መካከለኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመር በመጠገን ከትላንት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም የውቅሮና የአዲግራት ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ እየተሰራ ሲሆን፤ በቀጣይም በአክሱም እና በሽሬ ከተሞች ያለውን የዝቅተኛና መካከለኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ለመጠገን አስፈላጊ ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል፡፡  

በስፍራው የተሰማሩ የጥገና ባለሙያዎች አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎችን ታግለው ሌት ተቀን በመስራት አገልግሎቱ ወደ ቦታው እንዲመለስ ላደረጋችሁት ጥረት ተቋሙ ምስጋናውን ያቀርባል።

በቀጣይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማቶች ጠግኖ ሁሉንም የክልሉ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ አሁን ከተሰማራው ኃይል በተጨማሪ የተቋሙ ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተውጣጡ የቴክኒክ ባለሞያዎች ያየዘ ግብረ ኃይል በፍጥነት ወደ ሥፍራው ይልካል፡፡ 

ይህ ግብረሃይል በትግራይ ክልል ያሉትን የጥገና ባለሞያዎች የሚያግዝ፣ የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያስፈልገው አስፈላጊ ድጋፎች በመለየት የሚያቀርብና በአጭር ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ እንዲቻል ሁኔታዎችን የሚያመቻች ነው፡፡

በትግራይ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለአንድ ወር ያህል የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top