Connect with us

ፖሊስ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር አዋልኩኝ አለ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ

ወንጀል ነክ

ፖሊስ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር አዋልኩኝ አለ

ፖሊስ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር አዋልኩኝ አለ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት እና ኅብረተሰቡን ከጎኑ በማሰለፍ ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው ኦፕሬሽን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢየሱስ ገዳም እና ጦር ኃይሎች /ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን/ አካባቢ በሚገኙ ሁለት ስፍራዎች ላይ ተከማችቶ የነበረ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር አውሏል።

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እና ሀገርን የማፍረስ እኩይ ተልእኮውን ለማሳካት የተለያዩ የኢኮኖሚ አሻጥር መረቦችን ዘርግቶ ሲሠራ ቆይቷል።

በዚህ መሠረት ቀደም ሲል በተለያዩ 17 ቦታዎች ተከማችቶ በሕዝብ ጥቆማ እና በክትትል የደረሰበትን በብዙ ቢሊዮን ብር የሚገመት ብረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
ሰሞኑን ደግሞ ብረት አከማችተው የተገኙ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ውጤት የተገኘው በኅብረተሰቡ ትብብር በመሆኑ የፌዴራል ፖሊስ መረጃውን ላደረሱ ግለሰቦች ታላቅ ምስጋና ያቀርባል።

በቀጣይም ዜጎች ተመሣሣይ ጉዳዮች ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመሮች 987፣ 816፣ 991፣ እና በቢሮ ስልክ 0111110111 – አዲስ አበባ ፖሊስ፤ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀለ መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077 እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ስልክ ቁጥሮች – 0115309027፣ 0115309231፣ 0115309077 መረጃውን በማድረስ እና አጥፊዎችን በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።(ፌ/ፖሊስ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top