Connect with us

የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ

የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ
ፌደራል ፖሊስ

ወንጀል ነክ

የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ

የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ተያዘ

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኢንተርፖል ኦፕሬሽንና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዲቪዥን በህገ-ወጥ መንገድ በመኖሪያ ቤት የተከማቸ በርካታ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ ሰሞኑን ተይዟል፡፡

383 ጥቅል ቦንዳ ህገ ወጥ ልባሽ ጨረቁ በኮልፌ ቀራኒዮ ሎሚ ሜዳ አካባቢ ወረዳ 13 እና 14 እንዲሁም ውንጌት በረኪና ፋብሪካ ገባ ብሎ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባና በሶስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ተከማችቶ እንደተገኘ ኢንተርፖል ኦፕሬሽንና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዲቪዥን ሃላፊዋ ኢ/ር ጥሩወርቅ መንግስቴ ገልጸዋል፡፡

የቦንዳ ልብሱ ሊያዝ የቻለው የማህበረሰብ ጥቆማን መሰረት በማድረግ ከጉሙሩክ፣ከመድሃኒትና ቁጥጥር ባለስልጠናትጋር በጋራ ዳሰሳዊ ጥናት በማካሄድ እንደሆነ ኢንስፔክተሯ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

እንደኢንስፔክተሯ ገለጻ በቁጥጥር ስር የዋለው ቦንዳ ልብሰም ከ3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ግምት አለው፡፡

ህገ-ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ቡድኖችና ግለሰቦች ሀገሪቷ ከቀረጥ የምታገኘውን ገቢ በማሳጣትና ገብያው እንዳይረጋጋ ያደርጋሉ፡፡በኮንትሮባንድ የሚገቡ ቁሳቁሶችም የጤና ችግር ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ፡፡

በመሆኑም ከህብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግና የተለያዩ የመረጃ ስልቶችን በመጠቀም ያለ ህጋዊ ፍቃድ ማንናውንም አይነት ቁሳቁስ አከማችተው በሚገኙ ግለሰቦችና ቡድኖችን በቁጥጥር ስር በማዋል መርመራ በማካሄድ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በዚህም ህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው በተገኙ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ኢንስፔክተር ጥሩወርቅ ገልፀዋል፡፡

በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉና የገቢያ ሁኔታው እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ ነገሮችን ህብረተሰቡ  ሲመለከት  ለህግ አስከባሪ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንስስፔክተሯ አሳስበው ዜጎች ቤታቸውን ሲያከራዩ የተከራዩን ማንነትና ሰራ በሚገባ ሳያውቁ ቤታቸውን ቢያከራዩ ለሚፈጠሩ ወንጀሎች አከራዮች ከተጠያቂነት ስለማያመልጡ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል የሚል መልክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፖል የሀገር ውስጥ ኦፕሬሽንና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ከአባል ሀገራት ጋር በጋራ በመሆን በርካታ ወንጀሎችን በመከላከል ሰፊ ስራ ከመስራቱም በተጨማሪ የሀገራችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የኦፕሬሽን ስራዎችን ይሰራል፡፡(ፌደራል ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top