Connect with us

የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ 

የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ 
ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

ወንጀል ነክ

የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ 

የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ 

በአዲስአበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት የውንብድና ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ በእስራት ተቀጣ፡፡ 

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በቦሌ ክፍል ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 03-2421 ኦሮ የሆነ በተለመዶ አባዱላ ተብሎ የሚጠራውን መኪና እያሽከረከረ ግብረ አበሮቹን ይዞ ወደ ግል ተበዳይ ሽኩር የሱፍ ሱቅ በመሄድ አንደኛው ያልተያዘው ግብረ አበሩ ባለሱቁን “የ50 ብር ካርድ አለህ ወይ” ብሎ በመጠየቅ ካርዱን ሊሰጠው ወደ ውስጥ ሲገባ ያልተያዙት ሁለቱ ግብረ አበሮቹ ከመኪናው በመውረድ ተከትለው በመግባት አንደኛው ግብረ አበሩ በጩቤ አንገቱን ይዞ በማስፈራራት ሁለተኛው ግብረ አበሩ በሱቁ ውስጥ የነበረውን 30 ሺ ብር እና አጠቃላይ ከ51ሺ ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን ከወሰዱ በኋላ ተከሳሽ ይዞ በመሰወሩ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የከባድ ውንብድና ወንጀል ተከሷል።

ዐቃቤ ህግም እንደ ክሱ አቀራረብ የሰውን እና የሰነድ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ 

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና ሪከርድ የሌለበት መሆን ማቅለያ በመያዝ ጥቅምት 24 ቀን 3013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ7 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡(ፌ/ጠ/ዐ/ህግ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top