Connect with us

“አብዛኛው የአዲስአበባ ሕዝብ የምርጫ ካርድ አልወሰደም”

"አብዛኛው የአዲስአበባ ሕዝብ የምርጫ ካርድ አልወሰደም"
ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ዜና

“አብዛኛው የአዲስአበባ ሕዝብ የምርጫ ካርድ አልወሰደም”

“አብዛኛው የአዲስአበባ ሕዝብ የምርጫ ካርድ አልወሰደም”

በአዲስ አበባ እስከ አሁን የምርጫ ካርድ የወሰዱ መራጮች ብዛት አነስተኛ ነው ተባለ። ከተጀመረ ሶስተኛ ሳምንቱን ሊይዝ በተቃረበው የመራጮች ምዝገባ በርካታ ሰው አለመመዝገቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አስታውቋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የተመዘገበው ሰው ብዛት 200 ሺ 903 ብቻ እንደሆነ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል።

እስካሁን የተመዘገቡ የመራጮችን ቁጥር “አነስተኛ” ሲሉ የጠሩት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ “በነበሩት ቀናትና በነበሩት ጣቢያዎች ላይ ይሄ ብቻ መመዝገብ አልነበረበትም” ሲሉ ለፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ባደረጉት ገለጻ ላይ አስረድተዋል።

ቦርዱ ወደ 24 ሺህ ገደማ ምርጫ ጣቢያዎች እስካሁንም አለመከፈታቸውን በዛሬው ስብሰባ ላይ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ 1 ሺ 848 የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ 186ቱ አለመከፈታቸውን ቦርዱ ገልጿል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top