Connect with us

በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር ዋለ

በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ ብር በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ወንጀል ነክ

በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር ዋለ

በቂርቆስ ክ/ከተማ በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከባንክ ውጪ የሚገኙ በርካታ ብሮችን ወደ ባንክ እንዲገቡ በማድረግ የኢኮኖሚ ስርዓቱን ለማስተካከል እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ታሳቢ ባደረገ መንገድ የብር ኖት መቀየሩን ተከትሎ የሚፈፀሙ ህገ- ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ደንበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ከህዝብ ጥቆማ መምጣቱን የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ደጀኔ ጠቅሰዋል፡፡

ፖሊስም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት በንግድ ቤቱ ላይ ባደረገው ብርበራ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው መመሪያ ውጪ ተከማችቶ የተገኘ 2 ሚሊዮን 631ሺህ 735 አዲሱን እና ነባሩን የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡

መንግስት እና የፀጥታ አካላት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት የሚያከናውኑትን በህገ- ወጦች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባር በመደገፍ ህብረተሰቡ የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንስፔክተር ሰለሞን ደጀኔ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፡-አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top