Connect with us

የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ “ቅቡልነት የለውም”- የትግራይ ክልል

የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ "ቅቡልነት የለውም"- የትግራይ ክልል
BBC Amharic news

ዜና

የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ “ቅቡልነት የለውም”- የትግራይ ክልል

የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ  የፌዴሽን ምክር ቤት ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አፈ ጉባኤው፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት ከመስከረም 25፣ 2013 ዓ. ም. ጀምሮ የሥልጣን ዘመኑ ማብቃቱን በማጣቀስ፤ ያስተላለፈው ውሳኔ “ሕጋዊ መሠረት የለውም፤ ተቀባይነት የለውም፤ ተግባራዊም ሊሆንም አይችልም” ብለዋል።

ከክልል መንግሥት በታች ያሉ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ መዋቅሮችን የማደራጀት ሥልጣን የክልሉ መሆኑን የሚናገሩት አፈ ጉባዔው፤የፌደራል መንግሥት በቀጥታ ወደ ታች ወርዶ ሊሠራ የሚችልበት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም በማለት ውሳኔውን “የአሃዳዊነት አስተሳሰብና ተግባር” ሲሉ ኮንነዋል።

አፈ ጉባዔ ሩፋኤል፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ መሠረት የብሔር ብሔረሰቦች ወኪል ነው ካሉ በኋላ፤ በዋናነት ከየክልሎች የሚወከሉ አባላት ያሉበት ምክር ቤት መሆኑን ይገልጻሉ።

ምክር ቤቱ ሥልጣኑን ከሕገ መንግሥቱ ውጪ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ያራዘመ ስለሆነ፤ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ብለዋል።

“ምክንያቱም የክልል ምክር ቤቶችም ሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ማካሄድ አለባቸው” በማለት በቂ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ሰጥቶ ሥልጣኑን ያራዘመ ስለሆነ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ብለዋል።

ከዚህ በፊትም የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተወካዮቹ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደማይሳተፉ አስታውቋል። ለዚህም ምክንያቱ የምክር ቤቱ የሥልጣን ዘመን ስላበቃ፤ አዲስ ምርጫ ተደርጎ ክልሎች ወኪሎቻቸውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት መላክ ስላለባቸው መሆኑን አንስተዋል። (BBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top