Connect with us

በመተከል ዞን በንፁሀን ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 358 ሰዎች ተያዙ

በመተከል ዞን በንፁሀን ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 358 ሰዎች ተያዙ
Photo: Social media

ወንጀል ነክ

በመተከል ዞን በንፁሀን ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 358 ሰዎች ተያዙ

በመተከል ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተሳተፈዋል የተባሉ 358 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አበራ ባያታ÷ በቅርቡ በመተከል ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እናየሕግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉና የፌዴራል መንግስት በትኩረት እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከሰሞኑ በመተከል ዞን ቡለን እና ወምበራ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አየተሠራ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ የተለያዩ ተሳትፎዎችን አድርገዋል የተባሉ ተጨማሪ 30 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ አበራ ጨምረው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ተሳትፎ የነበራቸው 328 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ያስታወሱት አቶ አበራ÷ሰሞኑን በ2ቱ ወረዳዎች እየተሠራ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ ተጨማሪ 30 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

እስካሁን በተሠራው የህግ ማስከበር ሥራም ለችግሩ መፈጠረና መባባስ የተለያዩ ተሳትፎ የነበራቸው 358 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

ሰሞኑን በዞኑ ወምበራ ወረዳ የጸጥታ ችግር በተፈጠረባቸው ቀበሌዎች 1 የፖሊስ አባልን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ተባባሪ ነበሩ ተብለው የተጠረጠሩ 8 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

በተመሳሳይ በቡለን ወረዳ ኤጳር፣ አይጋሊና በዶሬ ቀበሌዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግርና ከደረሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ በቡለን ማዕከል ሆነው ሲተባበሩ የነበሩ 22 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር እንደዋሉ ገልጸዋል።

ሃላፊው አያይዘውም መንግስት በሁለቱ ወረዳዎች በንጹኃን ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ ኃይሎችን ለመደምሰስና በቀጥታም ሆነ በተለያየ መልኩ የተሳተፉ አካላትን በሕግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠራ ያለውን የሕግ ማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስታወቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top