Connect with us

ጃዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው

ጃዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው
Photo: Social media

ወንጀል ነክ

ጃዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው

ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ፍርድ ቤቱ ማንነታቸውን የማረጋገጥ ስራ የሰራ ሲሆን፥ በዚህ መሰረት አቶ ጃዋር እድሜያቸው 34 መሆኑን የፖለቲካ አመራር መሆናቸውን እና ባለትዳርና 1 ልጅ አባት መሆናቸውን እንዲሁም በሂዩማን ራይት ማስተርስ መያዛቸውን በአዲስ አበባ ኗሪ መሆናቸውን አስመዝግበዋል።

አቶ በቀለ ገርባም የአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን፤ መምህርና እድሜያቸው 60 ዓመት እንደሆነ እንዲሁም ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት መሆናቸውን አስመዝግበዋል።

ሌሎችም በተመሳሳይ ማንነታቸውን አስመዝግበዋል።

ከምክትል ኢንስፔክተር እስከ አምሳ አለቃ ደረጃ ማእረግ ያላቸው 6 ግለሰቦችም ማእረጋቸው በክሱ ባለመካተቱ ማረጋቸው እንዲመዘገብ አድርገዋል።

በሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያ ቤት የሚገኙት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና መስተዋርድ ተማም በችሎቱ አልቀረቡም።

እንዲሁም አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ብርሀነ መስቀል አበበ፣ ፀጋዬ አራርሳ ያልቀረቡ ሲሆን፥ በችሎት ለተጠራው የኦ.ኤም.ኤን ተወካይ የሆነ እኔነኝ ብሎ ያስመዘገበ ሰው የለም።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ላይ እንደየተሳትፏቸው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ፣ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል ነው መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215 አስር ተደራራቢ ክሶች ያስከፈተው።(FBC)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top