Connect with us

በቦሌ አርፖርት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ

በቦሌ አርፖርት ሰባት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ
Photo: Facebook

ወንጀል ነክ

በቦሌ አርፖርት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ

በቦሌ አርፖርት ሰባት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ።

ስናይፐሩ የተያዘው በተበታተነ መልኩ በቦርሳዎች ከሌሎች እቃዎች ጋር ተጠቅልለው እንደነበር ተገልጿል።

በቀን 25/12/12 በቦሌ ኤርፖርት አለማቀፍ በረራ መግቢያ በኩል ከሳዑዲ አረብያ የመጣ አንድ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጅዳ ጠቅልለዉ ወደ ሀገራቸዉ እንደሚገቡና የሚይዙት የግል መገልገያ ዕቃ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆንላቸዉ ደብዳቤ መያዛቸው ተገልጿል።

ግለሰቡ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ከግል መገልገያ ዕቃዎቻቸዉ ጋር ተገጣጥሞ ለ7 የስናይፐር ጦር መሳሪያ የሚሆኑ ክፍሎችን በታትኖ በተለያዩ ሻንጣዎች ዉስጥ ደብቀዉ ለማሳለፍ ሲሞክሩ በቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከድርጅቱ ሰራተኛ ሰምቷል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top